ክፍለ ጊዜ፡- 20/21
ገጽ 3/7: ርዕስ ሀ፡- ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለመውጣት እራሳችንን ማዘጋጀትርዕስ ሀ፡- ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለመውጣት እራሳችንን ማዘጋጀት
የስነ-ልቦና ደህንነትን መፍጠር
አስተማማኝ በሆነው የኤስ ኦ ኤስ መንደር ውስጥ ካለዎት ሥራ እና ከተለመደ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቹ መውጣት ጥርጣሬን እና ተስፋዎችን እንዲሁም ጭንቀቶችን ይፈጥራል። ከከፍተኛ ለውጥ ጋር እራሳችንን በምናላምድበት ወቅት ይህ ተፈጥሮአዊ እና ጤናማ የሆነ ምላሽ ነው። ከስነ-ልቦና አንጻር እዚህ ጋር የሚጠበቅብን ሞያዊ ተግባር አስተማማኝ ስፍራ ከሆነው የኤስ ኦ ኤስ መንደር ወጥተን እራሳችንን የቻልን የማህበረሰብ አሳዳጊዎች በመሆን አስተማማኝ የሆነ አዲስ ስፍራን መፍጠር ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ የምናደርገው ዝግጅት ዋነኛው አካል እያንዳንዱ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለመውጣት ደህንነት እና ምቾት እስከሚሰማው ድረስ በጋራ መወያየት እና ማቀድ ነው። ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
አንዲት የኤስ ኦ ኤስ እናት ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ከመውጣት በፊት ህጻናትን ማዘጋጀት ስለምንችልበት መንገድ እንደሚከተለው ትናገራለች።
ህጻናት ደህንነት የሚሰማቸው እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ደህንነት ሲሰማቸው ብቻ ነው
በእንክብካቤ ውስጥ ያሉ ህጻናት እና ታዳጊዎች የዕለት ተዕለት እንክበካቤ ሰጪዎቻቸው የሚሰሟቸው ስሜቶች በቀላሉ ተጽዕኖ ያሳድሩባቸዋል። እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ፍርሀቶች ካሉባቸው እና ለወደፊት ስለሚመጣው ለውጥ አብዝተው የሚጨነቁ ከሆነ በስራቸው ያሉት ህጻናት አስተማማኝ መሰረት የሆነ ተንከባካቢ አለኝ የሚለውን ስሜት ሊያጡት ይችላሉ። በመሆኑም ህጻናቱ እንደ መነታረክ፣ ያለመታዘዝ፣ ማዘን ወይም እንክብካቤ ሰጪው ላይ እምነት እንደማጣት ያሉ አስተማማኝ ያልሆነ ግንኙነት ባህሪያትን በማሳየት ምላሽ ይሰጣሉ። ጥርጣሬዎቹ እና ችግሮቹ በሙሉ ውይይት ተደርጎባቸው ካልተፈቱ በስተቀር አንድ እንክብካቤ ሰጪ በህይወቱ እና በስራው ላይ ከፍተኛ ለውጥ በሚያጋጥመው ጊዜ የተረጋጋ ለመምሰል አይችልም። ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
ሁላችንም ለለውጥ ምላሽ የምንሰጥበት መንገድ የተለያየ ነው
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ስለመውጣት ስናስብ ፍርሀት እንዲሁም የደስታ ስሜት አንድ ላይ ቢሰማን ተፈጥሮአዊ ነው። በቦትስዋና የሚገኙ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች የሰጧቸው ሁለት ምላሾች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
እናት ሀ፡- “በዚህ መንደር ውስጥ የኤስ ኦ ኤስ እናት ሆኜ ለ16 ዓመታት ፍቅር ስሰጥ ቆይቼአለሁ። ፍቅር የሞላበት ቤቴ ነው፤ ጓደኞቼ በሙሉ ያሉትም እዚህ ነው! የተለያዩ ጥያቄዎች በአእምሮዬ እየመጡ ስለምጨነቅ ሌሊት መተኛት አልችችም፡- ህጻናቱ ያለቅሱ ይሆን? አዲሶቹ ጎረቤቶቼ ይቀበሉኝ ይሆን? ገቢ የማመነጨው እንዴት ነው? ለአንደኛው ህጻን ሀኪም ቢያስፈልገኝስ፡- ማን ጋር ነው መደወል ያለብኝ፤ ማንስ ክፍያውን ይከፍለዋል? ምን አልባት ህይወት የተሻለ ይሆን ይሆናል
እናት ለ፡- “በጣም የእረፍት ስሜት ነው የተሰማኝ፤ የአደራ እናት እንደመሆኔ መጠን አሁን የራሴን ውሳኔዎች መወሰን እችላለሁ እንዲሁም ከዚህ በኋላ ከማህበረሰቡ ተለይቼ አልኖርም። እርግጥ ነው መንደሩ ውስጥ ያሉ ጓደኞቼ በሙሉ ይናፍቁኛል። ነገር ግን አዲስ የግንኙነት መረብ መዘርጋት እችላለሁ እንዲሁም ሞያዊ ክህሎቶቼን በማጋራበት ወቅት ጎረቤቶቼ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ዘመዶቼም አሁን በፈለግኩት ጊዜ መጥተው ሊጠይቁኝ ይችላሉ። ሁል ጊዜም አነስተኛ ንግድ የመጀመር ህልም ነበረኝ ስለዚህ አሁን ምን አልባት ላደርገው እችል ይሆናል። ልጆቼም አዳዲስ ጓደኞችን ለማፍራት በጣም ይጓጓሉ እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ሌሎች ህጻናት ጋር ሁሉ አንድ ዓይነት እንደሆኑ ይሰማቸዋል።”
ህጻናቱን ከማረጋጋታችን በፊት ለህጻናቱ ዜናውን ከመንገራችን አስቀድመን የእውነት የተረጋጋን፣ ተስፋ የሚሰማን እና ስሜትን ማገናዘብ የምንችል መሆን አለብን።
የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ቡድን መመስረት
ይህ ቡድን በሂደቱ ወቅት እራሳችሁን በደንብ ለማላመድ እንድትችሉ ጭንቀቶቻችሁን፣ ተስፋዎቻችሁን እና ዕቅዶቻችሁን በነጻነት ማጋራት የምትችሉበትን መድረክ የሚፈጥር ነው። ይህ ቡድን በማህበረሰቡ ውስጥ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ሆናችሁ በደንብ እስከምትደላደሉ ድረስ እስከ መጨረሻው መደበኛ የሆኑ ስብሰባዎች ይኖሩታል። ስብሰባዎቹ በአካባቢ የመልሶ መቀላቀል ቡድናችሁ ወይም የፌርስታርት አስተማሪ (Fairstart Instructor) ትምህርት በወሰደ አንድ ሠራተኛ ሊመራ ይችላል። በቡድኑ ውስጥ የሚገለጹ ነገሮች በሚስጥር መያዝ ይኖርባቸዋል። ለመጀመሪያ ስብሰባችሁ የሚሆን የአጀንዳ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
የ30 ደቂቃ የቡድን ውይይት፡- ተሞክሮዎቻችን እና ለወደፊቱ የምንጠብቃቸው ነገሮች
እባካችሁ ለግማሽ ሠዓት ያህል (ወይም ካስፈለገም ከዚያ በላይ) ገለጻ አድርጉ እንዲሁም ተወያዩ፡-
- የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ ሆናችሁ ለምን ያል ጊዜ ቆይታችኋል?
- የኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ በምትኖሩበት ወቅት በጣም የሚያስደስቷችሁ ጥቅማ ጥቅሞች ምድን ናቸው?
- ውስንነቶቹ ምንድን ናቸው (በዚህ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ ያጣችሁት ነገር ምንድን ነው)?
- ከአንድ (ምንም ጭንቀት የሌለበት) እስከ አምስት (በጣም ጭንቀት ያለበት) በሆነ መለኪያ ስትለኩት፡-
- ከመንደሩ ስለመውጣት ስታስቡ ምን ያህል ያስጨንቃችኋል?
- በማህበረሰቡ ውስጥ ስለመኖር በጣም የሚያስደስታችሁ ነገር ምን የሚሆን ይመስላችኋል?
- በዚህ ጉዞ ውስጥ ሀሳብ መለዋወጥ፣ መዘጋጀት እና መደጋገፍ የምንችለው እንዴት ነው?
ሁሉም ተሳታፊ በደንብ ዝግጁ እንደሆነ እስከሚሰማው ድረስ በእነዚህ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ መወያየት ያፈልጋል (ምን አልባትም በርካታ ስብሰባዎችን ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል)።
የሥራ ዕቅድ ርዕስ ሀ
እያንዳንዷ እናት ለሚቀጥለው ስብሰባ ለመዘጋጀት የግል የሥራ ዕቅድ ልታዘጋጅ ትችላለች፡-
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ስለመውጣት በቂ መረጃ ያለኝ፣ የተረጋጋሁ እና የተዘጋጀሁ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ በቡድኑ ውስጥ ውይይት ላደርግባቸው እና ላጠራቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው?
የሥራ ዕቅዶችን ካዘጋጃችሁ በኋላ እባካችሁ በርእስ ለ ዙሪያ ቀጣዩን የቡድን ስብሰባችሁን ለማድረግ ፕሮግራም ያዙ።