ክፍለ ጊዜ 10/21

ገጽ 5/7፡- ርዕስ ሐ፡- በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ስላሉት ባህሎች፣ የሥራ ድርሻዎች እና ባህሪ እንዲማር ህጻኑን ማገዝ

ርዕስ ሐ፡- በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ስላሉት ባህሎች፣ የሥራ ድርሻዎች እና ባህሪ እንዲማር ህጻኑን ማገዝ

ሁሉም ቤተሰብ የራሱ የሆኑ ልማዶች እና ባህሪን የሚመለከቱ ደንቦች (እርስ በእርስ የምንነጋገርበትን መንገድ፣ እርስ በእርስ የምንከባበርበትን መንገድ፣ በቤተሰቡ ውስጥ ያሉ የዕለት ተዕለት ተግባራትን እና የመሰሳሰሉትን የሚመለከቱ) አሉት። እያንዳንዱ የቤተሰቡ አባል “በቤተሰባችን ውስጥ የምናሳየው ባህሪ ይህ ነው” የሚለውን ነገር ስለሚያውቅ አብዛኛውን ጊዜ ፈጽሞ አንወያይባቸውም። ነገር ግን ከሌላ ቤተሰብ ወይም ከአንድ ተቋም ወይም ሊንከባከቡት ካልቻሉ ወላጆችም ጭምር የመጣ ህጻን በጣም ቀላሎቹን የሥነ-ምግባር ደንቦችም እንኳን መማር በጣም ሊከብደው ይችላል። የአደራ ልጁ የባህሪ ችግሮች ያሉበት ከሆነ የራሱ የአደራ ቤተሰቡ ልጆችም እንኳን የአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ ለምን እንክብካቤ ላይ ላለው ህጻን የተለየ ባህሪ አንደሚያሳዩት ለመገንዘብ ሊቸገሩ ይችላሉ።

የወላጆቻቸው ( የአደራ ቤተሰቡ የስጋ ልጆች) ትኩረት አዲስ የመጣው ህጻን ላይ ብቻ ነው ያለው በሚል ሊቀኑ ወይም ፍርሀት ሊያድርባቸው ይችላል። ምን አልባት ህጻኑ የሚያሳየው ባህሪ ሊያስቆጣቸውም ጭምር ይችላል (“ዘው ብሎ ገብቶ ሳይጠይቀኝ ልብሶቼን ይወስዳል!”).

ስለዚህ  ማመጣጠኛ አዲስ ዘዴ ማግኘት አስፈላጊ ነው። የአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ አዲስ የስነ-ምግባር ደንቦችን ሊያወጡ፣ ደንቦቹን ለሁሉም የቤተሰቡ አባላት ሊያስረዱ እና በዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረጉ ሊያሳዩ ይችላሉ። ይህን መደበኛ በሆነ መልኩ ማድረግ በእንክብካቤ ላይ ያለው ህጻን የቤተሰቡ አባል እንደደሆነ እንዲሰማው ይረዳል እንዲሁም ምን ዓይነት ባህሪ ማሳየት እንዳለበት ያስተምረዋል።

የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ያሉ ብዙ ህጻናት በቤተሰቡ ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር በምን መልኩ መስተጋብር ማድረግ እንዳለባቸው ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ ነው። ይህን እንዲማሩ ለመርዳት ምን ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ? ደንቦችን ለማውጣት እና ተግበራዊ ለማድረግ የሚረዱ ሀሳቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

አብሮ መስራት የሚቻልባቸውን መንገዶች የሚመለከቱ ደንቦችን ለማውጣት በየሳምንቱ መደበኛ የቤተሰብ ስብሰባዎችን ማድረግ። ቀለል ባለ መልኩ ለምሳሌ የሚከተለውን ጥያቄ በመጠየቅ ጀምሩ፡- እርስ በእርስ እንዴት መከባበር እንችላለን? ህጻናቱ በዚህ ውስጥ መሳተፋቸው እና መስማማታቸው አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፡-“እርስ በእርስ መረዳዳት ስለምንችልበት መንገድ ተወያይተን ሦስት ደንቦችን እናውጣ” ወይም “እራት ስንበላ በየተራ ቀናችን እንዴት እንደነበር እንነጋገር እንዴ?” ወይም “እርስ በእርስ ያሏችሁን ነገሮች እና አሻንጉሊቶች ብትጋሩ ጥሩ ነው” ወይም “አንድ ደንብ አለኝ፡- ሁላችንም በየተራ የመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ ሰሀን እናቅርብ”። ግጭቶችን ለመከላከል ይጠቅማል ብላችሁ የምታስቡትን ማንኛውንም ርዕሰ ጉዳይ ልትመርጡ ትችላላችሁ።

ምሳሌ፡-

ሁለት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆች በዕድሜ አነስ ያሉትን ልጆች እየተከታተሉ የግል ጊዜ እና ቦታ እንዳይኖራቸው ስለከለከሏቸው እንደተበሳጩ አንዲት የአደራ ቤተሰብ እናት አወቀች። በዚህ ጉዳይ  አንድ ምሽት ላይ ከአጠቃላይ ቤተሰቡ ጋር ከተወያየች በኋላ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉት ልጆች መቼ ብቻቸውን መተው እንዳለባቸው ደንብ አወጣች።

 

ይህ የኤስ ኦ ኤስን የወላጆች ስልጠና ከወሰደው ከጋሉስ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ነው። ጋሉስ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን ስለማሳደግ ያወራል እንዲሁም እንደ አባት ያሉበትን ኃላፊነቶች የተለያዩ ገጽታዎች በአጽንዖት ይገልጻል።

በቤተሰብ ውስጥ ሁል ጊዜም ያለመግባባቶች ይኖራሉ። ህጻናት ደንቦች መኖራቸውን እና መቼ እና እንዴት በደንቦቹ ላይ ድርድር ማድረግ እና በችግሮች ላይ መወያየት እንደሚችሉ ማወቃቸው አስፈላጊ ነው። ቀስ በቀስ ውይይቶቹ ህጻናቱ እንዴት አብረው መስራት እንደሚችሉ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይረዷቸዋል።

በጣም ውስጣቸው ለተረበሸ የአደራ ቤተሰብ ልጆች በምን መልኩ መስተጋብር ማድረግ እንዳለባቸው ለመማር ከተለመደው በላይ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል።

አንድ የሚፈልገውን ነገር በጣም የተነፈገን ህጻን አንድ ዓመት ተኩል ዕድሜ ላይ እያለ ከተቀበሉ የአደራ ቤተሰቦች ጋር የተደረገ አንድ ቃለ መጠይቅ እንደሚከተለው እንደምሳሌ ቀርቧል፡-

“እኛ ስንቀበለው ከሞላ ጎደል መንቀሳቀሰስ አይችልም ነበር፣ መናገር አልለመደም ነበር፣ እንዲሁም ገና ጡጦ ብቻ ነበር የሚጠባው። የራሳችን ልጆች አዲስ ታናሽ ወንድም ይኖረናል ብለው በጉጉት ሲጠብቁት ነበር፤ ነገር ግን ምላሽ ሊሰጣቸው አልቻለም ነበር። ሊነኩት ወይም ሊደባብሱት ሲሞክሩ መጮህ ይጀምር ነበር ወይም ሊቧጭራቸው ይሞክር ነበር። በቂ ማነቃቂያ ያላገኘ መሆኑን እና የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችን መጠን መጀመሪያ ለረጅም ጊዜ በእሱ ላይ መሥራት እንደነበረብን ልጆቻችን የተረዱት ረጅም ጊዜ ቆይተው ነበር።አብዛኛውን ጊዜ ማነቃቂያ እናደርግለት ስለነበር በጣም በፍጥነት ዕድገት ማሳየት ጀምሮ ነበር፤ ነገር ግን ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ እንዴት መስተጋብር ማድረግ እንዳለበት እንደማያውቅ ግልጽ ነበር፡- በጣም በኃይል የተሞላ፣ ኃይለኛ እና ሁል ጊዜም ቀዥቃዣ ነበር። ከአንድ ደቂቃ በላይ በአንድ ውይይት ወይም እንቅስቃሴ ላይ መቆየት አይችልም ነበር። አብዛኛውን ጊዜ እየሰራ የነበረውን ነገር ጥሎ ይሄድ ነበር ወይም ውይይት ላይ እያሉ ሌሎች ሰዎችን ያቋርጥ ነበር። ይፈራ እና ይጨነቅ ስለነበረ አብዛኛውን ጊዜ ሌሎች ሰዎችን ለመቆጣጠር እና ሁኔታውን በቁጥጥሩ ሥር ለማዋል ይሞክር ነበር። ልጆቻችን ከእሱ አምስት እና ስድስት ዓመት በዕድሜ ይበልጡ ስለነበር ድክ ድክ የሚል ህጻን የመመገቢያ ጠረጴዛው ዙሪያ ያሉትን ሰዎች ለመቆጣጠር እችላለሁ ብሎ ማሰቡ እና የሚፈልገውን ነገር ካላገኘ ዝም ብሎ መጮሁ በጣም ግራ ያጋባቸው ነበር። ስለዚህ በውይይት ወቅት እንዴት ተራውን መጠበቅ፣ ሌሎች ሰዎችን ማዳመጥ እና መልስ መስጠት እንዳለበት ለማስተማር ሙሉ ቤተሰቡ አብሮ መሥራት ነበረበት። በተጨማሪም የት መሄድ እንደሚችል እና እንደማይችል መገንዘብን እንዲማር ብዙ መመሪያ ያስፈልገው ነበር።አሁን ዘጠኝ ዓመቱ ነው ። ትምህርቱን ለመከታተል ችሏል፤ ነገር ግን በጣም ጠንካራ ስሜት ሲሰማው አሁንም የአራት ዓመት ልጅ ባህሪ ያሳያል። አሁን ሁሉንም የቤተሰቡን አባላት ያምናል፣ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኘውን ትልቁን ልጃችንን በጣም ይወደዋል እንዲሁም ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ እርዳታ መጠየቅን ለምዷል። አስተማሪዎቹ በጣም ቻይ ቢሆኑም በጣም ጥብቅ ናቸው፤ ስለዚህ ከበፊቱ በላይ በጣም በፍጥነት በመማር ላይ ነው። እኛም እንደ ቤተሰብ በጣም አስጨናቂ የሆኑ የዕለት ተዕለት ሁኔታዎችን ማስተናገድን እና ግጭቶችን አንዴት መከላከል እንዳለብን ተምረናል። በሆነ መልኩ ይህ እኛን፣ የራሳችንን ልጆች እና ሌላኛውን የአደራ ቤተሰብ ልጃችንን አቀራርቦናል፤ ነገር ግን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ለሁላችንም በጣም ከባድ ነበሩ።”

አስተያየት የሚሰጥባቸው እና ውይይት የሚደረግባቸው ጥያቄዎች

10 ደቂቃ

  • ተመሳሳይ ችግሮች ላሉባቸው የአደራ ቤተሰብ ልጆች እንክብካቤ ሰጥታችኋል?
  • ቤተሰባችሁ በምን መልኩ ነበር ምላሽ የሰጣቸው እና የመስተጋብር ክህሎቶችን ሊያስተምሯቸው የሚችሉ ሥራዎችን የሠራው?
  • እናንተ ሳትቀበሏቸው በፊት እንክብካቤ ባለማግኘታቸው የተነሳ እንዲህ ዓይነት ችግሮች ያሉባቸው ህጻናት ላይ በምን መልኩ መሥራት እንደሚያስፈልግ የሚጠቁሙ ምክሮች ወይም ተሞክሮዎች አሏችሁ?
  • ከሌሎች ጋር መስተጋብር ማድረግን እንዲማር ህጻኑን ለመርዳት ሙሉ ቤተሰቡ ተቀናጅቶ እንዲሠራ ለማድረግ በቤት ውስጥ ምን ዓይነት ሥራ ለመሥራት ዕቅድ አላችሁ?