ክፍለ ጊዜ 10/21

ገጽ 7/7 የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

እባካችሁ ከሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ አንዱን መርጣችሁ የሥራ ዕቅድ አውጡለት። አሁን ለምትሰሩት ሥራ በጣም ጠቃሚ የሆነውን ርዕሰ ጉዳይ ምረጡ።

  • ህጻኑ አስተማማኝ መሠረት እና የራሱ ጊዜ እና ቦታ እንዳለው እንዲሁም የአደራ ቤተሰቡ የራሱ ቤተሰብ እንደሆነ እንዲሰማው መሥራት። ይህ እንዴት ሊከናወን ይችላል?
  • በቤተሰቡ ውስጥ ያሉት ህጻናት በሙሉ ባህሪን በሚመለከቱ ደንቦች ላይ የሚወያዩባቸው እና ድርድር የሚያደርጉባቸው ሳምንታዊ ስብሰባዎችን በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ለማድረግ ዕቅድ ማውጣት። ይህን እንዴት ታደርጋላችሁ?
  • የአደራ ቤተሰብ ወላጆች፡- በማህበራዊ መረባችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎች ህጻኑን መረዳት እና ለሚያሳያቸው ባህሪዎች ምላሽ መስጠት የሚችሉባቸው ጥሩ መንገዶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ መወያየት። ማንን ታናግራላችሁ፤ መቼ?

የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን ምን እንደተወያያችሁ እና ምን ድምዳሜ ላይ እንደደረሳችሁ ጻፉ እንዲሁም ማን ምን እንደሚሰራ ወስኑ።

ፍላጎት ስላሳያችሁ እያመሰገንን እስከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ድረስ ለምትሰሩት ሥራ መልካም ዕድል እንመኝላችኋለን!