ክፍለ ጊዜ 14/21

ገጽ 2/7 በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ስላሉ ልጆች ያላችሁን ሞያዊ ዕውቀት መለየት

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ስላሉ ልጆች ያላችሁን ሞያዊ ዕውቀት መለየት

አንድ ህጻን በሚጎረምስበት እና አሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በሚገባበት ወቅት እንክብካቤ ሰጪዎች የሚጠብቋቸው ነገሮች እና የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? ከራሳችን የወጣትነት ዕድሜ ቀድሞውንም ያገኘናቸው ጠቃሚ ልምዶች አሉን።

ይህ የመጀመሪያ መልመጃ ከጉርምስና ጋር ተያይዘው በሚመጡ ተግዳሮቶች ዙሪያ የራሳችሁን ተሞክሮዎች በተመለከተ ሁለት ሁለት በመሆን የሚደረግ ቃለ መጠይቅ ነው። በዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ውስጥ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ለመገንዘብ እና በእነሱ ላይ ለመሥራት እነዚህን ተሞክሮዎች እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ በየቡድናችሁ ትወያያላችሁ።

መልመጃ፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሆነን ራሳችን ካሳለፍነው ጊዜ በመነሳት ምን እናውቃለን?

ሁለት ሁለት በመሆን የሚደረግ ቃለ መጠይቅ

20 ደቂቃ

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠቀም ሁለት ሁለት ሆናችሁ እያንዳንዳችሁ ለ10 ደቂቃ እርስ በእርስ ቃለ መጠይቅ ተደራረጉ።

  1. ከልጅነት ወደ አዋቂነት ራሳችሁ ካደረጋችሁት ሽግግር ጋር በተያያዘ የነበራችሁ ተሞክሮ ምን ይመስል ነበር?
  2. ከዕድሜ እኩዮቻችሁ ጋር የነበራችሁ ማህበራዊ ግንኙነት በምን መልኩ ተቀየረ?
  3. በሰውነታችሁ ላይ ከነበሩት አካላዊ ለውጦች ጋር በተያያዘ የነበራችሁ ተሞክሮ ምን ይመስል ነበር?
  4. ከወላጆቻችሁ/ከእንክብካቤ ሰጪዎቻችሁ ጋር በተያያዘ አስተሳሰባችሁ፣ ባህሪያችሁ እና አመለካከታችሁ የተለወጠው በምን መልኩ ነበር?
  5. ወላጆቻችሁ እና ሌሎች አዋቂዎች እናንተን ለመርዳት ምን አደረጉ (ካደረጉት ነገር ውስጥ ያልጠቀማችሁ ምን ነበር)?
  6. እንደ ማጠቃለያ፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያላችሁ እናንተን ከማሳደግ ጋር በተያያዘ ለወላጆቻችሁ በጣም ከብዷቸው የነበረው ነገር ምንድን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

የቡድን ውይይት

15 ደቂቃ

ልምዳችሁን በመጠቀም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች ላይ ለሚሰሩ እንክብካቤ ሰጪዎች አስፈላጊ የሆኑ ሦስት ወሳኝ እሴቶችን ተወያይታችሁ ጻፉ።

እሴት 1፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆቻችን            እንድናሳያቸው ያስፈልጋል (ለምሳሌ አክብሮት እና መረዳት፣ አመራር፣ ሥርዓት)።

እሴት 2፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆቻችን ከእኛ            ይፈልጋሉ።

እሴት 3፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆቻችን ከእኛ           ይፈልጋሉ።