ክፍለ ጊዜ14/21

ገጽ 5/7 ስለ ጉርምስና አሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ካሉ ልጆች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች

ስለ ጉርምስና አሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ካሉ ልጆች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች

ስለ የስሜት መቀያየሮች እና አካላዊ ለውጦች የሚደረጉ ውይይቶች

ከልጆቻችሁ ጋር ስለ ጉርምስና ከተወያያችሁ እና ከትንሽ ዕድሜ ጀምሮ ካዘጋጃችኋቸው ከልጅነት ወደ አዋቂነት ስለሚያደርጉት ሽግግር ጉርምስና ውስጥ ሲገቡ መወያየት ቀላል ይሆናል። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ መሆን በጣም ለጉዳት ተጋላጭ የሚያደርግ ጊዜ ሊሆን ስለሚችል በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ብዙ ልጆች ግልጽ አርአያዎች እና ሚስጥራቸውን ሊያዋዩአቸው የሚችሏቸው አዋቂዎች ያስፈልጓቸዋል።

በሰውነት ላይ እንደሚከሰቱ ለውጦች፣ እንደ ያለመተማመን ስሜቶች፣ የግብረ ሥራ ግንኙነት እና የወደፊት ህልሞች ስላሉ ከጉርምስና ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ካሉ ልጆች ጋር ለመወያየት የሚያስችል ቅርርብ መፍጠር ጊዜ ይወስዳል። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጅ ሚስጥሩን የሚያካፍለው ሰው የግድ ዋና እንክብካቤ ሰጪው/ዋ መሆን የለበትም/የለባትም። ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ያሉ አንዳንድ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች ተመሳሳይ ጾታ ያለው ሰውን ማናገር ይበልጥ ሊቀል እንደሚችል ይናገራሉ። ስለዚህ ሚስጥራቸውን የሚያጋሩት ሰው አጎታቸው፣ አክስታቸው፣ አያታቸው ወይም ማህበራዊ ሰራተኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ዋናው ነገር በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጅ ሊያምነው እና ስለ ህልሞቹ እንዲሁም ስለሚያጋጥሙት ተግዳሮቶች ሊያናግረው የሚችለው አዋቂ ሰው ያለው መሆኑ ነው።

ጉርምስና ላይ በነበርኩበት ወቅት እያለፍኩበት ስለነበረው ነገር የኤስኦኤስ እናቴን ለማናገር ምቾት አይሰማኝም ነበር። ነገር ግን አዋቂን ማናገር በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ላናግረው የምችለው ወንድ የኤስኦኤስ ሠራተኛ አግኝቼአለሁ። በጣም ነበር የረዳኝ። –

አንድሪው፣ 21 ዓመት

የቡድን ውይይት
የመልመጃ ሀሳብ፡- የግል ታሪክ
15 ደቂቃ

  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁን ለማነጋገር ስትሞክሩ ተግዳሮት የሚሆንባችሁ ነገር ምንድን ነው?
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁ ምክንያታዊ በማይሆንበት ጊዜ ምላሽ መስጠት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ማሳወቅ የማያስፈልጋቸው የግል ጉዳይ ምንድን ነው እንዲሁም ደህንነታቸው መጠበቁን ለማረጋገጥ ሲባል የግድ ለእናንተ ሊያሳውቋችሁ የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው 
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ካለ ልጃችሁ ጋር መስማማት የምትችሉት እንዴት ነው? ይህም የቤቱ ሕጎች ላይ የመስማማት አንድ አካል ሊሆን ይችላል።
  • በተጨማሪ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላለ ልጃችሁ ጥሩ የውይይት አጋር ይሆናል ብላችሁ የምታስቡት ሰው (ዘመድ ወይም ጓደኛ) አለ?
በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጅ ስለራሱ ስለሚያስባቸው ነገሮች የግል ታሪክ ወይም ዳያሪ እንዲያረቅ ሀሳብ አቅርቡ፡- ስለ ጥርጣሬዎቹ፣ ህልሞቹ፣ ችግሮቹ እና ምኞቶቹ ማለት ነው። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጃችሁ ራሱን ችሎ ለመኖር ከቤተሰቡ በሚወጣበት ወቅት የምትሰጡት ቅጂ ማስቀመጥ የሚለውን አስቡበት።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች አመራር መስጠት የምትችሉት እንዴት ነው? ስለ ፍቅር፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚደረጉ ውይይቶች

ብዙ የአደራ ቤተሰቦች ልጆቻቸው አሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሲገቡ በተወሰነ መልኩ አቅመ ቢስነት ይሰማቸዋል። የት ነው የሚሄዱት? ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት ከማን ጋር ነው? የፍቅር እና ወሲባዊ ግንኙነቶች ውስጥ ናቸው? ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው? ስለዚህ ነገር መነጋገር የምንችለው እንዴት ነው?

ከማስገደድ እና ሕጎችን ከማስቀመጥ ይልቅ እንክብካቤ ሰጪ እንደመሆናችሁ ባሉባችሁ አንዳንድ ፍርሀቶች እና ስጋቶች ውስጥ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁን በተወሰነ መጠን ብታሳትፉት ጥሩ ነው። ይህም በተለይ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ሴት ልጆችን በተመለከተ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ከወንድ ዕኩዮቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ በርካታ ጉዳዮች ላይ የደህንነታቸው ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። በኬንያ የአደራ ቤተሰብ እናት የሆነችው ካትሪን ታሪኳን እንደሚከተለው ታካፍላለች፡-

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆቻችን ከትምህርት ቤት ወጥተው የከፋ ድህነት ያለባቸው ሰፈሮች ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ደህንነታቸው አስተማማኝ አይደለም። በተለይም ደግሞ ሴት ልጆቻችን። ወንዶቹን ልጆች ትንሽ ዕድሜ ላይ እያሉ ለአዋቂነት ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ለልጆቼ ትምህርት እሰጣቸዋለሁ እንዲሁም ጥበቃ ሳይደረግላቸው ሲቀር እና ራሳቸውን ሳይጠብቁ ሲቀሩ ምን ዓይነት ችግር ሊፈጠር እንደሚችል አሳያቸዋለሁ እንዲሁም አስረዳቸዋለሁ። አንዳንድ ጊዜ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉት ሴት ልጆች “አስፈሪ” ምሳሌ ሊሆናቸው የሚችል ታሪክ ያለው ሰው ፈልጌ እጠቀማለሁ። ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲሁም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ስለሚተላለፉ በሽታዎች እና በጉርምስና ወቅት በሰውነት ላይ ስለሚከሰቱ ለውጦች ማውራት በጣም አስፈላጊ ነው። ከሴትም ከወንድም ልጆች ጋር ማለት ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከራሴ የጉርምስና ዕድሜ የተወሰዱ ምሳሌዎችን እጠቀማለሁ።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች አመራር መስጠት የምትችሉት እንዴት ነው? ስለ ፍቅር፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚደረጉ ውይይቶች
በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ካለ ልጃችሁ ጋር ጥሩ ውይይት ለማድረግ እነዚህን ሦስት እርምጃዎች እና የመወያያ ርዕሶች መጠቀም ትችላላችሁ። ይህም ቀስ በቀስ በጣም ጥንቃቄ ስለሚሹ ጉዳዮች ግልጽ በሆነ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አስተማማኝ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል።
እርምጃ 1፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከሚገኙ ልጆች ጋር ስለ ጉርምስና ማውራት

በጉርምስና ወቅት ስለሚፈጠሩት ነገሮች ዕውቀት ማስጨበጫ ብዙ መንገዶች አሉ። አንዳንድ ጊዜ በቤተሰቡ ውስጥ ያሉ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን አንድ ላይ አድርጎ ማነጋገር አግባብ ሊሆን ይችላል፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እያንዳንዱን በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጅ ለየብቻ ማነጋር ተመራጭ ሊሆን ይችላል። ቀለል ያለ ጊዜ (ለምሳሌ የቤት ውስጥ ሥራዎችን አብራችሁ ስትሰሰሩ) መርጣችሁ ብታደርጉት በጣም ቀላል ይሆናል። አንዳንድ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ አብረው ተቀምጠው ሻይ ወይም ቡና እየጠጡ እያሉ ማድረጉ ጥሩ ተሞክሮ ይሆንላቸዋል። ለአንዳንድ ሰዎች አንድ የግል ታሪካቸውን በመናገር መጀመር በጣም ሊቀላቸው ይችላል።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጅ እንዲህ ላለው ውይይት ዝግጁ እንደሆነ እና ከእናንተ ጋር ባለው ግንኙነት ውስጥ መተማመን እንደሚሰማው ማስተዋል አስፈላጊ ነው። ለማዳመጥ እና ለማውራት ዝግጁ መሆናችሁን በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላለው ልጅ ንገሩት እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጅ ከሌላ አዋቂ ጋር ወይም ሌላ ጊዜ ላይ ቢያወራ ይበልጥ ደህንነት የሚሰማው ከሆነ ያንን እሺ ብላችሁ ተቀበሉ።

ስለ ጉርምስና እና ሰውነቴ ላይ እየታዩ ስለነበሩት ብዙ ለውጦች ከእናቴ ጋር ማውራት ደስ አይለኝም ነበር። እናቴ ግን ጊዜ ስለሰጠችኝ በሂደት ላናግራት ዝግጁ ሆንኩኝ። ለሌሎች ወላጆች የምሰጣቸው ምርጥ ምክርም ይኸው ነው፡-በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች ጊዜ እና ቦታ ስጧቸው።

– ጄን፣ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለች ልጅ

እርምጃ 2፡- መታለፍ ስለሌለባቸው መስመሮች፣ ስለአክብሮት እና ስለወደፊት ህይወታቸው አውሩ

አማራጭ እንክብካቤ ላይ ያሉ ብዙ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች ከዕኩዮቻቸው ግሩፖች ለሚደርስባቸው ግፊት በተለይ ተጋላጭ በመሆናቸው ደህንነቱ አስተማማኝ ያልሆነ ድርጊት ይፈጽማሉ። ይህም አብዛኛውን ጊዜ በህጻንነታቸው ባሳለፉት አሰቃቂ ተሞክሮ የተነሳ ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት ስለሚሰጡ ነው። አንዳንዶቹ በግሩፑ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ምንም ነገር ያደርጋሉ። ከእኩዮቹ ግሩፕ ግፊት እየተደረገበት እንደሆነ ሲሰማው የማይታለፉ መስመሮችን የማስቀመጥ መብት ያለው ስለመሆኑ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁን ማነጋገር አስፈላጊ ነው።

እንክብካቤ ሰጪዎች እንደመሆናችሁ መጠን እራሳችሁ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከነበራችሁበት ጊዜ የተወሰዱ ምሳሌዎችን በመጠቀም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለውን ልጅ ልታነጋግሩት እና አጋጥመዋችሁ የነበሩ ፈታኝ ሁኔታዎችን ልታካፍሉት ትችላላችሁ። ለምሳሌ ከዕኩዮቻችሁ ጋር የነበራችሁ ግንኙነት ምን ሆነ? ከዕኩዮቻችሁ ጫና ደርሶባችሁ ነበር? ከወላጆቻችሁስ?

አደገኛ የሆኑ ተግባራትን “አልፈልግም” ማለት የሚችልባቸው መንገዶችን እንዲያገኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁን አግዙት እንዲሁም ለእሱ ትክክል እንደሆነ የሚሰማውን ነገር መለየት እንዲችል ድጋፍ አድርጉለት። ከዕኩዮቻቸው ከሚደርስባቸው ማጓጓት ጋር የተያያዙ አደገኛ ድርጊቶች ለወደፊት ተስፋቸው እና ህልማቸው እንቅፋት የሚሆኑ ከሆነ እምቢ ማለት እንዲችሉ አግዟቸው። የወደፊት ህይወታቸው ምን እንዲመስል እንደሚፈልጉ አዋሯቸው። ሁሉም ህልም ጥሩ ህልም ነው። እናንተ ለእነሱ የወደፊት ህይወት ያላችሁ ህልም የተለየ ሊሆን ይችላል፤ ግን ምንም ችግር የለውም። ዋናው ነገር በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለው ልጅ እናንተ እንደምትደግፉት የሚሰማው እና ሁል ጊዜም ከጎኑ ሆናችሁ ሳትፈርዱበት አመራር እንደምትሰጡት ማወቁ ነው።

ለመድገም ያህል፡- በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁ ሌላ አዋቂን ማናገርን የሚመርጥ ከሆነ ያንን ውሳኔውን ደግፉ።

14 ዓመቴ እያለ በአካባቢው ያለ አንድ ማህበራዊ ሰራተኛ አለማማጄ ሆኖ ነበር። እስከ አሁን ድረስ አናግረዋለሁ። አለማማጄ የህይወቴ ምሰሶ ነው። ቤቴን ቀጥ አድርጎ ያቆመው እሱ ነው። ፒተር፣ 22 ዓመት
እርምጃ 3፡- ስለቤተሰብ ምጣኔ እና የወሊድ መቆጣጠሪያ አውሩ

እርምጃ 1 እና 2 መተማመን እና ግልጽነት እንዲኖራችሁ ካደረጓችሁ ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት እና የስነ ተዋልዶ ጤና እንዲሁም ኮንዶም እና የወሊድ መቆጣጠሪያ ስለመጠቀም ልታወሩ ትችላላችሁ፤ ይህም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች በጣም ጥንቃቄ የሚጠይቅ ርዕሰ ጉዳይ ነው።

የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚመለከተው እርግዝናን እና በግብረ ሥራ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን መከላከልን ነው። ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ እና ደህንነቱን መጠበቅ ስለሚችልበት መንገድ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጃችሁን ልታነጋግሩት ትችላላችሁ። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ጋር ስለተያያዙ ባህሪዎች እንድታሳውቁ ሊያነሳሷችሁ የሚችሉ ተጨማሪ ሀሳቦችን የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡- ./1-1_sexual-behaviour-and-contraception/

ምን አልባትም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁን እንድታናግሩ ሊረዷችሁ የሚችሉ የተወሰኑ ልምዶች ያሏቸው ሰዎችን በማህበረሰባችሁ ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ? በጣም በልጅነታቸው ልጅ የወለዱ ሰዎች፣ ከኤች.አይ.ቪ ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች፣ ወዘተ ማለት ነው።

 

በእንክብካቤ ላይ ያሉ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን ያለዕድሜያቸው ለማርገዝ እና በግብረ ሥጋ በሚተላለፉ በሽታዎች ለመጠቃት አብዛኛውን ጊዜ የሚዳርጋቸው የዕውቀት ማነስ እና ግልጽ ውይይቶችን ያለማድረግ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። በመሆኑም እራሳቸውን መጠበቅ ስለሚችሉበት መንገድ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች ማሳወቅ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው። እራሳችሁ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያላችሁ ከነበራችሁ ተሞክሮ የተወሰዱ ምሳሌዎችን ወይም ከማህበረሰቡ የተወሰዱ ምሳሌዎችን ልትጠቀሙ ትችላላላችሁ። ምን አልባት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን ሰብስቦ ሊያሳውቃቸው የሚችል ነርስ ታውቃላችሁ? በዚህ ፈታኝ ወቅት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች አመራር ለመስጠት ምርጡ መንገድ ከእውነተኛ ህይወት የተወሰዱ ምሳሌዎችን መጠቀም እና ግልጽ አቅጣጫ መስጠት ነው። አንድ በኬንያ የሚገኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ልጅ እንዲህ ብሏል፡- እኛን በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለን ልጆችን ካለማቋረጥ አነጋግሩን እንዲሁም ስንሳሳት አርሙን። አመራር ማግኘት በከፍተኛ ሁኔታ ያስፈልገናል።

አስተውሉ፡- እንክብካቤ ላይ ያሉ ህጻናት በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ እያሉ ልጅ የመውለድ እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች የመጠቃት እጅግ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው መሆኑን እና በእንክብካቤ ላይ ያሉ ሴት ልጆች ብዙ ጊዜ ያለአባት ልጃቸውን የሚያሳድጉ እናቶች እንደሚሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ። ይህን እየጨመረ በመምጣት ላይ ያለ ችግር በአካባቢያችሁ ባህል ውስጥ ካሉ እሴቶች ጋር በጥንቃቄ ማጣጣም ያስፈልጋል። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዴት እና መቼ ማሳወቅ ትችላላችሁ የሚለው በአብዛኛው የሚወሰነው በአካባቢያችሁ ያለውን ባህል መሠረት በማድረግ ነው። በአንዳንድ ባህሎች ውስጥ ይህ ለምሳሌ በአደራ ቤተሰብ እናት እና በአደራ ቤተሰብ ሴት ልጇ መካከል ያለ በጣም ሚስጥራዊ ጉዳይ ነው፤ ውይይት ሊደረግበት የሚችለውም ፍጹም ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ነው። በሌሎች ባህሎች ውስጥ ደግሞ አንድ ወንድ እንክብካቤ ሰጪ ወይም አንድ ነርስ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ጥቂት ወንድ ልጆችን ሰብስቦ ሊያሳውቃቸው ይችላል፤ ወይም አንዲት ሴት በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ያሉ ጥቂት እህትማማች ልጆችን ሰብስባ ልታሳውቃቸው ትችላለች። የሚከተለውን ጽሁፍ ካነበባችሁ በኋላ እባካችሁ የአካባቢያችሁን ባህላዊ ደንቦች ባከበረ መልኩ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች ማሳወቅ እንደምትችሉ እና መቼ ማሳወቅ እንደምትችሉ በጥንቃቄ ተወያዩ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ሀሳቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

ሴት ልጆችን ስለ ንጽህና፣ የወር አበባ፣ ወሲባዊ ግንኙነቶች እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ማነጋገር አስፈላጊ ነው። ሴት ልጆቼን በማነጋግርበት ወቅት ከራሴ ህይወት ወይም ከጎረቤቶቼ ህይወት የተወሰዱ ምሳሌዎችን መጠቀም በጣም ያግዘኛል። ሮዝ፣ የአደራ ቤተሰብ እናት
ከሴት ልጆች ጋር በተያያዘ ስለሚያሳዩት ባህሪ ወንድ ልጆቼን ብዙ ጊዜ አዋራቸዋለሁ። የምናውቃቸው ሌሎች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች በተለይም ደግሞ በልጅነት ከማርገዝ ጋር በተያያዘ ያጋጠሟቸውን ሁኔታዎች እንደ ምሳሌ እጠቀማለሁ። እንዲህ ያሉትን ሁኔታዎች እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ማወቅ ስለሚያስፈልጋቸው ማናቸውም ዓይነት ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ሁል ጊዜም ወደ እኛ ወደ ወላጆቻቸው በመምጣት ሊያናግሩን እንደሚችሉ እነግራቸዋለሁ። አን፣ የአደራ ቤተሰብ እናት
የቡድን ውይይት

30 ደቂቃ

  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች የማይታለፉ መስመሮችን ማስቀመጥ እንዴት ከባድ ሊሆን ይችላል? በተለይም ደግሞ ዕኩዮቻቸው እናንተ የማትፈቅዷቸውን እንቅስቃሴዎች በሚያደርጉበት ወቅት?
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን ስለ ጉርምስና ልታነጋግሯቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁን ለወደፊቱ ስለሚመኟቸው ነገሮች ልታነጋግሯቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁን ስለቤተሰብ ምጣኔ እና የወሊድ መቆጣጠሪያ ልታነጋግሯቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ኮንዶም ስለመጠቀም ልታሳውቋቸው ከወሰናችሁ፡- የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ስለሚመለከቱ ጉዳዮች በግልጽ ከመወያየት ጋር የተያያዙ ሀይማኖታዊ ወይም የግል ችግሮች አሉ? ከአካባቢያችሁ ባህል ጋር እንዲጣጣም አድርጋችሁ በማስተካከል በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን ከጉዳት ሊጠብቋቸው የሚችሉ መፍትሄዎችን ማግኘት የምትችሉት እንዴት ነው?