ክፍለ ጊዜ 14/21

ገጽ 7/7 የሥራ ዕቅድ

የስራ እቅድ፡ ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚደረጉ ነገሮች

  • መተማመንን እና ግልጽነትን የሚፈጥር እንክብካቤ ሰጪ መሆን የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ከህጻን ልጆቻችሁ ጋር እንዲሁም በኋላ ላይ አሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ሁነኛ ውይይት እና መደበኛ በሆነ መልኩ በየጊዜው የሚደረግ የሀሳብ ልውውጥ መፍጠር የምትችሉት እንዴት ነው?
  • በቤታችሁ ውስጥ ካሉት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆች ጋር ያለውን መተባበር ልታሻሽሉ እና ጥሩ ግንኙነቶችን እና ስምምነቶችን መፍጠር የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ልጃችሁን ወይም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ጎረምሳ ልጃችሁን የማይታለፉ መስመሮችን በግልጽ በማስቀመጥ ከመጥፎ ጓደኛ ጋር መግጠምን እንዲከላከል ልትረዱት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ስለ ጉርምስና፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና ስለ ሰውነት ውይይቶችን መጀመር የምትችሉት እንዴት ነው?

እባካችሁ ዕቅዳችሁን እና ሀሳቦቻችሁን ጻፏቸው፡- ምን፣ መቼ እና የት እንደምታደርጉ ማለት ነው።

በዚህ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለምትሰሩት ሥራ እናመሰግናለን። እናንተ የምትሰሩት ሥራ በወጣቶቹ የወደፊት ህይወት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

በሥራችሁ ላይ መልካም ዕድል እንመኝላችኋለን!