ክፍለ ጊዜ 20/21

ገጽ 6/7 ፡- ርዕስ መ፡- ለህጻናት እና ለወጣቶች የሚደረግ የተጨባጭ ክህሎቶች ማዳበሪያ

፡- ርዕስ መ፡- ለህጻናት እና ለወጣቶች የሚደረግ የተጨባጭ ክህሎቶች ማዳበሪያ

 

በርዕስ ውስጥ ህጻናት እና ወጣቶች በማህበረሰቡ ውስጥ መኖርን በደንብ እንዲላመዱ የሚረዱ ሀሳቦች እና ተግባራት ቀረበዋል።

እንክብካቤ ከመቀበል እራስን ወደመቻል

በማህበረሰብ ውስጥ መኖር ከጀመሩ በኋላ ስለሚኖር ጤናማ ዕድገት የሙከራ ጥናቶች ምን ይነግሩናል?

የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ማህበራዊ ትስስሮችን ከመመስረት ጋር የተያያዙ ክህሎቶችን ያዳብራሉ። አንዳንዶቹ የራሳቸውን አነስተኛ ንግድ በመጀመር የቁጠባ ማህበራት ውስጥ ይገባሉ፣ ወዘተ። በኤስ ኦ ኤስ መንደር ውስጥ አገልግሎቶችን ከመስጠት እና የዕለት ተዕለት ተግባራትን ከማከናወን በማህበረሰቡ ውስጥ ወደመኖር የሚያደርጉት ሽግግር መጀመሪያ ላይ ለልጆቻቸው በጣም ፈታኝ ሊሆን ይችላል (በተማሯቸው ክህሎቶች ላይ ለአዲሱ ከባቢ ሁኔታ አስፈላጊ የሆኑ ማተካከያዎችን ማድረግ ይኖርባቸዋል)። በሂደት ይህ ተሞክሮ ራሳቸውን መቻልን እንዲማሩ ያደርጋቸዋል። ህጻናቱ በፍጥነት ራሳቸውን ማላመድን መማር ይኖርባቸዋል እንዲሁም ጓደኞችን ማፍራት እና ማናቸውንም አዳዲስ ክህሎቶች ጠንቅቀው ማወቅ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ብዙ ጥርጣሬዎች ይኖሯቸዋል (በገበያ ውስጥ በምግብ ዋጋ ላይ ስለሚደራደሩበት መንገድ፣ እንሰሳትን ስለሚንከባከቡበት መንገድ፣ አውቶብስ ስለሚሳፈሩበት መንገድ፣ ወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያ ስለሚከፍሉበት መንገድ፣ ወዘተ)።

የአፍሪካ ባህሎች፡- ህጻናት ተጨባጭ ክህሎቶችን የሚማሩበት ሁነኛ መንገድ

በልማዳዊ የመንደር ባህሎች ውስጥ ህጻናት በተፈጥሮ የዕለት ተዕለት ክህሎቶችን የሚማሩት ከአፍላ ህጻንነታቸው ጀምሮ ነው። እርሻ ዘላቂነት ያለው ነበር እንዲሁም አካባቢን ለመንከባከብ ቦታ ይሰጥ ነበር። አዋቂዎቻቸው እና ታላቅ ወንድም እህቶቻቸው የሚያደርጓቸውን ነገሮች ያዩ እና ደግመው ያደርጉ ነበር  እንዲሁም እንደየእድሜአቸው ሥራ ያግዙ ነበር። በሥራ እና በመዝናኛ ሠዓት መካከል ምንም ክፍፍል አልነበረም፡- ዘፈን፣ ጭፈራ እና ወቅት ጠብቀው የሚመጡ በዓላት የአጠቃላይ ህይወታቸው አካል ነበሩ።

የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ትልቅ ዋጋ ያለውን ባህላዊ ዕውቀታቸውን የማህበራዊ እና የተጨባጭ ክህሎቶች ስልጠና ለመስጠት መጠቀም የሚችሉት እንዴት ነው?

ተጨባጭ ክህሎቶችን እና ግንኙነቶች ላይ መስራትን ማቀናጀት

በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ህጻናት የቤተሰቡ የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ በንቃት ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው። ይህ ማለት ግን የቤቱን ስራ ሁሉ መስራት አለባቸው ማት አይደለም። ለእያንዳንዱ ህጻን የቤት ውስጥ ሥራዎችን፣ ትምህርትን እንዲሁም ጨዋታ እና እረፍትን አመጣጥኖ ማስኬድ አስፈላጊ ነው። የዕለት ተዕለት ክህሎቶችን ከማስተማር ጎን ለጎን እንክብካቤ ሰጪዎች ግንኙነቶች ላይ መስራት ይችላሉ። የመተማመን ስሜት እንዲሰማቸው ስለ ስሜቶቻቸው፣ ጭንቀቶቻቸው፣ ህልሞቻቸው እና ሀሳቦቻቸው አነጋግሯቸው። ይህን በምናደርግበት ወቅት ከእንክብካቤ ከወጡ በኋላ የሚያስፈልጓቸውን ተጨባጭ ክህሎቶች ይማራሉ እንዲሁም ኩራት እና ኃላፊነት ይሰማቸዋል።

ጨቅላ ህጻናትን፣ ህጻናትን እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናትን ማስተማርን የተመለከቱ ምሳሌዎች እዚህ ጋር ቀርበዋል፡-

ከለጋ ዕድሜ ጀምሮ የክህሎት ስልጠና መስጠት!

ጨዋታ እና መዝናናት ህጎችን እና ክህሎቶችን በመማር ረገድ ግንባር ቀደሙን ቦታ የሚይዙ ጉዮች ናቸው። ይህች የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ አንድ ህጻን የመተማመን ስሜት እንዲሰማው እሱ የሚያደርገውን ነገር አስመስላ ማድረግን ትጠቀማለች። የእሷን ስሜቶች እና ድርጊት ማስመሰልን እንዲሁም ከሌላ ሰው ጋር እንዴት መስተጋብር ማድረግ እንዳለበት ታስተምረዋለች። ይህም አስተማማኝ የሆነ መሠረት እንዳለው እንዲሰማው ያደርገዋል፤ ስለዚህ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በዙሪያው ያለውን ዓለም ለማሰስ እና እግር ኳስ መጫወትን ለመለማመድ የሚያስችል የደህንነት ስሜት ይሰማዋል።

 

 

በዕድሜ አነስ ላሉ ህጻናት የሚሆኑ ክህሎቶች እና ጨዋታዎች

በዕድሜ አነስ ያሉ ህጻናት ላይ የምትሰራ አንዲት የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ እዚህ ጋር ቀርባለች። ተጨባጭ ክህሎቶችን እንዲማሩ ከመምራት ጎን ለጎን ስለምታስተምራቸው አዳዲስ ክህሎቶች ኩራት እንዲሰማቸው አስደሳች የሆኑ ወሬዎችን ታዋራቸዋለች (የራሳችንን ልብስ ማጠብ)።

ከክህሎት ስልጠና ጎን ለጎን የተለመዱ የጨዋታ እንቅስቃሴዎች ህጻናትን እንደሚያስቋቸው እና በህይወታቸው ደስተኛ እንዲሆኑ እንደሚያደርጓቸው ታውቃለች። ጨዋታ ህጻናት አካላዊ ጥንካሬን እንዲያዳብሩ፣ ሰውነታቸውን እንዲቆጣጠሩ እንዲሁም ማህበራዊ መተጋገዝን እና ቀላል ህጎችን መከተልን እንዲማሩ ያደርጋል። መጠቀም የምትችሏቸው በርካታ ባህላዊ የአፍሪካ ጨዋታዎች እዚህ ጋር ቀርበዋል።

 

 

በዕድሜ ተለቅ ላሉ ህጻናት እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ህጻናት የሚሆኑ ክህሎቶች እና እንቅስቃሴዎቸ

ህጻናት እያደጉ ሲመጡ የክህሎት ስልጠና የግብረ ገብ እሴቶችን ከመማር እና ጠቃሚ ሞያዎችን በመማር እና እራስን መከላከል የሚችሉበትን መንገድ በማወቅ ከእንክብካቤ በኋላ ለሚመጣው ህይወት ከመዘጋጀት ጋር ይጣመራል። እዚህ ጋር አንድ ልምድ ያላቸው አባት (የአደራ እንዲሁም የስጋ አባት የሆኑ) አርአያ በመሆን ለወጣቶች የህይወት አመራር ስለመስጠት ይነግሩናል።