ክፍለ ጊዜ 21/21

ገጽ 1/6፡- ህጻናትን ከትውልድ ቤተሰባቸው ጋር መልሶ መቀላቀል

ህጻናትን ከትውልድ ቤተሰባቸው ጋር መልሶ መቀላቀል

 

የፕሮግራም ሥራ አስኪያጆች እና የኤስ ኤስ እናቶች ይህን መመሪያ እንድታነቡ በትህትና እንጠይቃለን

የርዕስ መግቢያ

ይህ ክፍለ ጊዜ አንድን ህጻን ወይም ወጣት ከትውልድ ቤተሰቡ ጋር መልሶ በመቀላቀል ሂደት ውስጥ ከሚሳተፉ አካላት በሙሉ ጋር ለሚደረጉ ተከታታይ ስብሰባዎች የሚያገለግል ደረጃ በምዕራፍ ተከፋፍሎ የተቀመጠ ማዕቀፍን የያዘ ነው። ስብሰባዎቹ የሚደረጉት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር የመልሶ መቀላቀል ፕሮግራም ሥራ አስኪያጆች እና በኤስ ኦ ኤስ እናቶች ስብስብ መካከል ነው። የሚከተሉት አራት የክፍለ ጊዜ ርዕሶች በዕቅድ ዝግጅታችሁ ውስጥ የምትከተሏቸውን አራት ምዕራፎች የሚገልጹ ናቸው፡-

ርዕስ ሀ፡- መልሶ መቀላቀልን የተመለከተ መግቢያ

ርዕስ ለ፡- የኤስ ኦ ኤስ እናቶች እና ሠራተኞች ለለውጡ መዘጋጀት የሚችሉት እንዴት ነው?

ርዕስ ሐ፡- የህጻኑን ግንኙነቶች እና ቁርኝቶች ለይቶ ማስቀመጥ

ርዕስ መ፡- ከመንግስት ሠራተኞች፣ ከማህበረሰቡ እና ከቤተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት

ርዕስ ሠ፡- ቤተሰቡ መልሶ ከተዋሀደ በኋላ ክትትል በማድረግ ስጋቶቸን መቀነስ

ልምምድ የሚደረግባቸው ብቃቶች/ችሎታዎች

  • መልሶ መቀላቀልን እና የቤተሰብ መልሶ መዋሀድን የተመለከተ እውቀት
  • በሂደቱ ውስጥ የኤስ ኦ ኤስ እናቶች፣ ህጻናት እና ዘመዶቻቸው ደህንነት እንዲሰማቸው ለማድረግ የሚረዱ ክህሎቶች
  • የአንድን ህጻን የአሁን እና የወደፊት የግንኙነት ቁርኝቶች መገምገም
  • ከመንግስት ሠራተኞች፣ ከማህበረሰቡ እና ከቤተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት
  • በመልሶ መቀላቀል ወቅት የሚከሰቱ የተለመዱ የስጋት መንስኤዎችን መቀነስ 

የክፍለ ጊዜው ዓላማ

ይህ ክፍለ ጊዜ አብራችሁ ለመስራት እና በኤስ ኦ ኤስ መንደር ውስጥ ከመኖር ህጻናት ከወላጆቻቸው ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ስኬታማ በሆነ መልኩ መልሰው ወደ መዋሀድ ለሚያደርጉት ስነ-ልቦናዊ እና የግንኙነት ሽግግር ለመዘጋጀት የሚረዳችሁ ይሆናል።