ክፍለ ጊዜ 15/21
ገጽ 3/7 በእንክብካቤ ውስጥ ካለፉ እና ልምድ ያላቸው ወጣቶች ምን ልንማር እንችላለን?በእንክብካቤ ውስጥ ካለፉ እና ልምድ ያላቸው ወጣቶች ምን ልንማር እንችላለን?
በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ከሚናገሩት ነገር ምን ልንማር እንችላለን? ሳንድራ የተባለችው በእንክብካቤ ውስጥ ያለፈች ወጣት በዚህ ረገድ ልምዳቸውን ካካፈሉ ወጣቶች ውስጥ አንዷ ናት። ከእንክብከካቤ ከወጣች በኋላ በዩኒቨርሲቲ ትምህርቷ ላይ እጅግ በጣም ጥሩ ብቃት አሳይታለች። ነገር ግን በትርፍ ጊዜ የሚሰራ ሥራ ስትፈልግ የአንድ ሥራ አገናኝ ቢሮ እጅ ላይ ወደቀች እና ወደ መካከለኛው ምስራቅ ላካት። በዚያም በቤት ሠራተኝነት ስትለፋ የቆየች ሲሆን ከቤት ሠራተኛ ይልቅ ባሪያ ነበረች ቢባል ይቀላል። በኋላ ላይ እንደምንም ብላ በማምለጥ ከብዙ ችግር በኋላ አሁን በጎዳና ላይ ቻፓቲ (ቂጣ) በመሸጥ መተዳደር ጀምራለች።
በእንክብካቤ ውስጥ ያለፈችው ኢውኒስ ልምዷን መሠረት በማድረግ በእንክብካቤ ውስጥ ላለፉ ወጣቶች እና ለእንክብካቤ ሰጪዎች ምክር የምትሰጥበትን ይህን ቪዲዮ በጥንቃቄ ተመልከቱት።
የቡድን ውይይት
- ሳንድራ ሥራ አገናኝ ቢሮው እንደሚያሳስታት ማወቅ ያልቻለችው ለምን ይመስላችኋል?
- ቃለ መጠይቁ ላይ ኢውኒስ የምትሰጠው ዋናው ምክር ምንድን ነው?
- በእንክብካቤአችን ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ከሚያጋጥሟቸው ዋና ዋና ስጋቶች ጋር በተያያዘ የራሳችን ተሞክሮ ምን ይመስላል?