ክፍለ ጊዜ 15/21

ገጽ 5/7 በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ከእንክብካቤ ከመውጣታቸው በፊት በጊዜ ማዘጋጀት

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ከእንክብካቤ ከመውጣታቸው በፊት በጊዜ ማዘጋጀት

ከሳሌህ ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ እንደሰማችሁት ኤስ ኦ ኤስ በእንክብካቤ ውስጥ ላለፉ ወጣቶች ባዘጋጀው መደበኛ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባዎች ላይ ተሳትፏል። በእንክብካቤ ውስጥ ካለፉ ወጣቶች ጋር ባደረግናቸው ቃለ መጠይቆች ውስጥ ወጣቶቹ ለሠራተኞች የሰጧቸው ምክሮች እንደሚከተለው በአጭሩ ቀርበዋል፡-

  • በእንክብካቤ ላይ ያሉ ህጻናት እና ወጣቶች በእንክብካቤ ውስጥ ካለፉ ወጣቶች ወይም በአማራጭ እንክብካቤ ውስጥ ካልሆኑ ሌሎች ወጣቶች ጋር እንዲገናኙ አድርጉ።
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉትን ልጆች እንዴት ለራሳቸው ኃላፊነት እንደሚወስዱ በማሳየት አዘጋጇቸው።
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ልጆች ኑሮአቸውን ለመደጎም በማህበረሰቡ ውስጥ መሥራት የሚችሏቸውን ሥራዎች አስተምሯቸው።
  • ለወጣቶች ግልጽ አመራር እና ከእውነተኛ ህይወት የተወሰዱ ምሳሌዎችን ስጧቸው።
  • በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ካሉ ቁልፍ ሰዎች ጋር አስተዋውቋቸው።
  • ቡድኖችን በመሰብሰብ ስለተለያዩ ጉዳዮች ውይይቶችን አድርጉ እንዲሁም ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን እና በእንግድነት የተጋበዙ ባለሞያዎችን (ወንጀልን ከመከላከል፣ ያለዕድሜ ማርገዝን ከመከላከል፣ ከኤች.አይ.ቪ. እና ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ልምድ ያላቸው ሰዎችን) ተጠቀሙ።”

በአሥራዎቹ ዕድሜ ወስጥ የሚገኙ ልጆችን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው? ለማቀድ ሊረዷችሁ የሚችሉ አንዳንድ ሀሳቦች
/strong>

በእንክብካቤ ውስጥ ላለፉ ወጣቶች ከተዘጋጁ ፕሮጀክቶች የተወሰዱ ለሥራችሁ መነሻ ሊሆኗችሁ የሚችሉ የተወሰኑ ሀሳቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

  • ሴሚናሮች እና ስብሰባዎች ላይ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር ሠራተኞች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን በተለያዩ የሥራ ቡድኖች መከፋፈል ይችላሉ። ከዚያም ከእንክብካቤ በኋላ በሚኖራቸው ህይወት ውስጥ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ተግዳሮቶችን እና አጣብቂኞችን መግለጽ። እያንዳንዱ ቡድን አንድን ጉዳይ እንዲያጠና፣ እንዲወያይ እና ከዚያም ለታዳሚው መፍትሄዎችን እና የመቋቋሚያ ስትራቴጂዎችን እንዲያቀርብ መጠየቅ። ገለጻው ከቀረበ በኋላ ሠራተኞቹ አዳምጠው ግብረ መልስ ሊሰጡ ይችላሉ። በተጨማሪም በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ እና ልምድ ያላቸው ወጣቶች ግብረ መልስ እንዲሰጡ ሊጋበዙ ይችላሉ።
  • በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ የዕደጥበብ ባለሞያዎች እና ሠራተኛ ሴቶች ሥራዎቻቸውን እና ክህሎቶቻቸውን እንዲያቀርቡ ሊጋበዙ ይችላሉ፤ ወይም አንድ የአደራ ቤተሰብ በአካባቢው ካለ የንግድ ባለቤት ጋር ሊገናኝ ይችላል። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች በአካባቢው ባለ አንድ የሥራ ቦታ ለተወሰነ ጊዜ በመሥራት ከእንክብካቤ ከወጡ በኋላ የኑሮ ወጪአቸውን የሚሸፍኑበት ሥራ ሊሆናቸው እንደሚችል ማየት ይችላሉ።
  • እንክብካቤ ካበቃ በኋላ በተለይ ወጣት ሴቶች የሚያጋጥማቸው አንደኛው አደጋ አብዛኛዎቹ ከእንክብካቤ ከወጡ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ያለአባት ልጃቸውን የሚያሳድጉ እናቶች መሆናቸው ነው። ስለ የግብረ ስጋ ግንኙነት እና የስነ ተዋልዶ ጤና እንዲሁም ጥንቃቄ ስለተሞላበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ከወጣቶች ጋር ለምታደርጓቸው ውይይቶች መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦችን ከሚከተለው ክፍለ ጊዜ ማግኘት ትችላላችሁ፡- (./1-1_sexual-behaviour-and-contraception/ )።

ራሱን የቻለ አዋቂ ወደመሆን የሚደረገውን ሽግግር በደስታ መቀበል

  • በአፍሪካ ባህል ውስጥ ከህጻንነት የአዋቂ የሥራ ድርሻዎችን እና ኃላፊነቶችን ወደመቀበል ለሚደረገው ሽግግር የሚረዱ የሽግግር ሥነ-ሥርዓቶች እና ድግሶች አሉ። እነዚህ ሥነ-ሥርዓቶች ልጁ አሁን ራሱን የቻለ አዋቂ መሆኑን ለወጣቱ እንዲሁም ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ግልጽ የሚያደርጉ ናቸው። ሽግግሩን የሚያበስር ማህበራዊ ዝግጅት ማዘጋጀት ለዚህ የስነ-ልቦና ለውጥ ዕውቅና ለመስጠት የሚረዳ ወሳኝ ዘዴ ነው። የልጁን የመጨረሻ የእንክብካቤ ቀን ለማክበር ፓርቲ ማዘጋጀት ትችላላችሁ (እንዲህ ያለው የማይረሳ ዝግጅት ራሱን የቻለ አዋቂ በመሆኑ በማንነቱ እንዲኮራ ወጣቱን ይረዳዋል)። የስንብት ፓርቲ ማዘጋጀት የአንድን ወጣት ራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ አቅም ያጠናክራል። ከዚህ አስቀድመው እንክብካቤ ሰጪዎች ወጣቱ በእንክብካቤ ካሳለፈው ጊዜ ጋር የተያያዙ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን እና ሌሎች የግል ቀረጻዎችን በአልበም መልኩ ማሰባሰብ አለባቸው። ዋና እንክብካቤ ሰጪው/ዋ አጭር ንግግር ሊያዘጋጅ/ልታዘጋጅ እና ወጣቱ/ቷ በእንክብካቤ ላይ እያለ/ች ለቤተሰቡ ወይም ለቡድኑ ህይወት ምን ዓይነት አስተዋጽኦ እንዳደረገ/ች ማውራት ይችላል/ትችላለች። የወጣቱን/ቷን ማህበራዊ ክህሎቶች፣ ጠንካራ ጎኖች እና ተሰጥኦዎች ማብራራት ይችላል/ትችላለች። ወጣቱም/ቷም በእንክብካቤ ላይ በነበረበት/ችበት ወቅት ስለተማራቸው/ተማረቻቸው ነገሮች እና ለወደፊቱ ስላቀዳቸው/ቻቸው ነገሮች ንግግር ማድረግ ይችላል/ትችላለች። ሌሎች ወጣቶች ወይም ህጻናት ደግሞ ግለሰቡ/ቧ እንዴት ጥሩ ጓደኛ እንደሆነ/ች ማብራራት ይችላሉ። የቤተሰቡ አባላት እና በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ የወደፊት ትውውቆች ሊጋበዙ እና ከፓርቲው በኋላ ለወደፊቱ ወጣቱን እንዴት ሊደግፉት እንደሚችሉ ሊወያዩ ይችላሉ።
  • የቡድን ውይይት

    10 ደቂቃ

    • ልጆችን ከእንክብካቤ ከመውጣታቸው ረጅም ጊዜ አስቀድመን ስለሚኖሩት ስጋቶች በማሳወቅ ልናዘጋጃቸው እና በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ልናገናኛቸው የምንችለው እንዴት ነው?
    • ለራሳቸው የሚሰጡትን ግምት እና በአዲሱ ህይወታቸው የሚጠቅሙ አዋቂዎች መሆናቸውን በሚያጎለብት መልኩ ከእንክብካቤ ለሚወጡ ወጣቶች ፈንጠዚያ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

    በህጻንነት፣ በአሥራዎቹ ዕድሜ እንዲሁም ወጣቱ አስተማማኝ መሠረቱን በሚሰናበትበት ወቅት ከእንክብካቤ እንዲወጣ በምን መልኩ ማዘጋጀት እንደሚቻል አጥንታችኋል። አሁን ደግሞ እንክብካቤ ካበቃ በኋላ ወደ ማህበረሰቡ መመለስን በምን መልኩ ማቀድ እንደሚቻል እንመለከታለን።