ክፍለ ጊዜ 15/21

ገጽ 7/7 የሥራ ዕቅዳችሁን መንደፍ

የሥራ ዕቅዳችሁን መንደፍ

እባካችሁ የሥራ ዕቅዳችሁ ላይ ተወያዩ፣ የሥራ ዕቅዳችሁን ንደፉ እንዲሁም ጻፉ፡- ምንድን ነው የምናደርገው፣ ማን ነው የሚያደርገው እና የምናደርገውን ነገር መገምገም የምንችለው እንዴት ነው? አንድ ወይም ከዚያ በላይ የዕድሜ ምድብ ወይም ርዕሰ ጉዳይ መርጣችሁ በዚያ ላይ የሥራ ዕቅድ ልታዘጋጁ ትችላላችሁ።

ለህጻናት

  • ህጻናት ማህበረሰቡን እንዲያውቁ በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ያለውን የዕለት ተዕለት ህይወት በምን መልኩ ማደራጀት እንችላለን?
  • ለህጻናት መሰረታዊ ክህሎቶችን ለማስተማር እና ራሳቸውን ችለው የራሳቸውን ግምገማዎች እንዲያደርጉ እና የራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲወስኑ ለማበረታታት የምንሰራው በምን መልኩ ነው? ወጣቶች የራሳቸውን ውሳኔ ሊወስኑ የሚችሉበትን ሁኔታ የምንፈጥረው እና በውሳኔያቸው መሠረት የምንንቀሳቀሰው እንዴት ነው?

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ ልጆች

  • ኑሮአቸውን መደጎም የሚችሉባቸውን ቀላል የሥራ ክህሎቶች እንዲማሩ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆቻችንን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
  • ከእንክብካቤ በኋላ ስለሚኖሩ ተግዳሮቶች ልናሳውቃቸው የምንችለው እንዴት ነው? (ቢቻል እባካችሁ ጥንቃቄ የተሞላበት የግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚመለከት መረጃ አካቱበት)።

  • ራሳቸውን የቻሉ አዋቂዎች የሚሆኑበት አዲስ ህይወት መጀመራቸው የሚከበርበትን ዝግጅት ለማዘጋጀት ማቀድ የምንችለው እንዴት ነው?

  • ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር እና የአደራ ቤተሰብ ወላጆች በመተባበር በተሳካ ሁኔታ የወጣቱ ታማኝነት እና ምሪት ወደ ሌላ አካል እንዲሸጋገር ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው?

እንክብካቤ ካበቃ በኋላ ማለማመድ (Mentoring) እና ከዕድሜ እኩዮች ጋር ጥምረት መፍጠር

  • አለማማጆች (mentors) እና በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች መገናኘት ያለባቸው በየስንት ጊዜው ነው?
  • ለወጣት ወንዶች እና ሴቶች ምድቦቹን ማዘጋጀት ያለብን አንድ ላይ ነው ወይስ ለወንዶች ወንድ አለማማጆችን (mentors) እና ለሴቶች ደግሞ ሴት አለማማጆችን (mentors)  በማድረግ ለየብቻ ነው?
  • እባካችሁ ልዩ አለማማጆች (mentor)እና ወጣቶች ለሚያደርጉት ስብሰባ የመጀመሪያ ረቂቅ አጀንዳ አዘጋጁ። እናንተ ባላችሁ ተሞክሮ መሰረት በጣም አስፈላጊ የሆኑት የውይይት ርዕሰ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች እና የፌርስታርት ፋውንዴሽን ሰራተኞች ይህን ክፍለ ጊዜ መንደፍ እንዲቻል ተሞክሮዎቻችሁን እና ምክራችሁን ስላጋራችሁን እናንተን እንዲሁም ህጻናቱን እና ወጣቶቹን ያመሰግናሉ። በተጨማሪም ከእንክብካቤ መውጣትን በተመለከተ ለሰጡን ጠቅላላ ቅኝት የምስራቅ አፍሪካ የምርምር ባለሞያዎችን እናመሰግናለን።