ክፍለ ጊዜ 15/21

ገጽ 4/7 ከጨቅላ ህጻንነት ዕድሜ ጀምሮ ክህሎቶችን እና ራስን መቻልን ማሰልጠን

ከጨቅላ ህጻንነት ዕድሜ ጀምሮ ክህሎቶችን እና ራስን መቻልን ማሰልጠን

የአካባቢያቸው ማህበረሰብ አካል ሳይሆኑ ላደጉ ወጣቶች ከእንክብካቤ መውጣት በጣም ከባድ ነው። በቃለ መጠይቆች ውስጥ የኤስ ኦ ኤስ እናቶች “እኛም ልጆቹም የሚሰማን ከማህበረሰቡ እንደተነጠልን ነው” ብለውናል። እንክብካቤ ላይ ላሉ ህጻናት ጥበቃ ከማድረግ ጎን ለጎን በአካባቢያቸው ባህል ውስጥ እንዲያድጉ ማገዝ ያስፈልጋል የሚለው ሀሳብ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ እየተስፋፋ ይገኛል። በየአካባቢው ያሉ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች/አሳዳጊዎች/ እና በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩ የኤስ ኦ ኤስ እናቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ትስስር እንዲፈጥሩ ወጣቶችን ማገዝ የሚቀላቸውም ለዚህ ነው።

 

የሚከተለው ለዚህ አንድ ምሳሌ ነው፡-

ህጻናት እና እንክብካቤ ሰጪዎች የማህበረሰቡ ተፈጥሮአዊ አካል እንዲሆኑ ለማስቻል ሲባል በርካታ የኤስ ኦ ኤስ ህጻናት መንደር እናቶች በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል ከነበረው የአንድ አጥር ግቢ ኑሮ ወጥተው የአደራ ቤተሰብ እናቶች በመሆን ላይ ይገኛሉ። እዚህ ጋር አንዲት ልምድ ያላት የኤስ ኦ ኤስ እናት እሷ እና ልጆቿ ተጨባጭ ክህሎቶችን ማዳበር እንዴት ደስ እንደሚላቸው ስታስረዳ ማየት ትችላላችሁ፡-

ማቱሊፖ ስትል እንደሰማችሁት ልጆቿ ገና ከአሁኑ በማህበረሰቡ ውስጥ ጓደኞች አሏቸው። የማቀድ እና ዶሮዎችን እና አንቁላል ለሽያጭ የማዘጋጀት ክህሎቶችን በቀላሉ በመማር ላይ ናቸው እንዲሁም መሸጥን እና በጀት ማዘጋጀትን ይማራሉ። ይህ ከማህበረሰቡ ጋር የሚደረግ የዕለት ተዕለት ግንኙነት በኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደር ወይም የአደራ ቤተሰብ ውስጥ በሚያድጉበት ጊዜም እንዲሁ ሊከናወን ይችላል። ህጻናት በማህበረሰቡ ህይወት ውስጥ መሳተፍን ሊለምዱ ይገባል። በአካባቢው ማሀበረሰብ ውስጥ የሚሳተፉ እንክብካቤ ሰጪዎች ካሏቸው እና ህጻናቱን በየቀኑ ይዘዋቸው የሚሄዱ ከሆነ በወጣትነት ጊዜ  የሚደረገው ሽግግር በአንጻሩ በጣም ቀላል ይሆናል።
የቡድን ውይይት
20 ደቂቃ

ህጻናት በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ህጻናት ጋር መተዋወቅ እና መጫወት የሚችሉት እንዴት ነው?

  • ህጻናትን ከእንክብካቤ በኋላ ለሚኖረው ጊዜ ለማዘጋጀት በእንክብካቤ ላይ እያሉ ምን ክህሎቶችን ልናስተምራቸው እንችላለን?
  • ለምሳሌ፡- የቤቱን የሳምንት በጀት ማዘጋጀት፣ ምግብ ወደሚሸጥበት ቦታ ሄደው አስቤዛ መግዛት፣ ምግብ ማብሰል፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን መክፈል፣ የህዝብ መጓጓዣዎችን መጠቀም መልመድ? እባካችሁ ከእንክብካቤ በኋላ የሚኖረውን ህይወት ለመቋቋም ምን ክህሎቶች ያስፈልጋሉ የሚለውን በተመለከተ ራሳችሁ ያሏችሁን ሀሳቦች ተጠቀሙ።

    ከእንክብካቤ በኋላ ለሚኖረው ጊዜ ልጆችን ለማዘጋጀት የሚያድጉበትን መንገድም እንዲሁ የግድ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል፡- የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እናደርግላቸዋለን እንዲሁም ውሳኔዎቻቸውን እንወስንላቸዋለን ወይስ ከዚያ በተጨማሪ ራሳቸውን ችለው የራሳቸውን ውሳኔ መወሰንን እናሰለጥናቸዋለን?

 

ትዕዛዝ ከሚያከብሩ ህጻናት ራሳቸውን ወደቻሉ ወጣቶች

በባህሉ መሠረት ወላጅ ስልጣን አለው ሲባል አብዛኛውን ጊዜ ትርጉሙ ህጻናት ትዕዛዝ ማክበር አለባቸው፣ ከአዋቂዎች ጋር ሲሆኑ ካልተጠየቁ በስተቀር ማውራት የለባቸውም እንዲሁም ሁል ጊዜም የሚነገራቸውን ነገር ማድረግን መልመድ አለባቸው ማለት ነው። ነገር ግን በእንክብካቤ ላይ ያሉ ህጻናትን ለአዋቂነት ለማዘጋጀት የራሳቸው አስተያየት እና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው የግድ ሊሰለጥኑ ይገባል። ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? ህጻናት ገና ከትንሽ ዕድሜያቸው ጀምሮ እንክብካቤ ሰጪዎች እንደሚያዳምጧቸው፣ ለአስተያየታቸው ቦታ እንደሚሰጡ፣ ጭንቀቶቻቸውን እንደሚጋሩ እና እንደሚወያዩ እና የራሳቸውን መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚረዷቸው የግድ ሊያውቁ ይገባል። መረጃን መሰረት በማድረግ የራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲወስኑ፣ የሚያሳልፏቸው ተሞክሮዎች ያሏቸውን አደጋዎች እና ጥቅሞች እንዲመዝኑ እና በግልጽ በመወያየት ውጤቶቻቸውን እንዲገመግሙ እንክብካቤ ሰጪዎች ህጻናትን ሊያበረታቷቸው ይገባል። ከማስገደድ ይልቅ ጥያቄዎችን መጠየቅ እና ማዳመጥ ጥሩ ነው።

ሳሌህ የተባለውን በእንክብከካቤ ውስጥ ያለፈን ወጣት አዳምጡት። በማደግ ላይ እያለ የኤስ ኦ ኤስ እናቱ ተስፋ ስለሚያደርጋቸው እና ስለሚያስባቸው ነገሮች ታናግረው የነበረ ሲሆን በጋራ ያደረጓቸው እነዚህ ውይይቶች አስተማማኝ መሰረትን ሰጥተውታል። በዚህም የተነሳ ከእንክብካቤ መውጣትን አይፈራም ነበር። ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ሰው ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱ ሊገጥሙት ስለሚችሉት ተግዳሮቶች በተጨባጭ እውነታውን በጣም ያገናዘበ እይታ አለው እንዲሁም ሊሚቋቋማቸው የሚችልበትን ዕቅድ አዘጋጅቷል።

የቡድን ቃለ መጠይቅ
በህጻንነት ክህሎቶችን ለማስተማር ማቀድ

ሁለት ለሁለት፣ 15 ደቂቃ

  • ወላጆቻችሁ ምን ተጨባጭ ክህሎቶችን አስተምረዋችኋል?
  • ያዳምጧችሁ እና የራሳችሁን ውሳኔዎች እንድትወስኑ ያበረታቷችሁ ነበር?
  • በአሁኑ ወቅት ህጻናትን የምታሳድጉት እንዴት ነው (ራሳችሁ ካደጋችሁበት መንገድ በምን መልኩ ይለያል)?
  • ህጻናትን ልናዳምጣቸው እና በዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ውስጥ ውሳኔዎችን መወሰን እንዲችሉ ልናግዛቸው የምንችለው እንዴት ነው?
እባካችሁ በህጻንነት ክህሎቶችን ለማዳበር እና ህጻናት የራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲወስኑ ውይይት ለማድረግ የራሳችሁን ተሞክሮ እና ሀሳቦች ተጠቀሙ። እንደ መነሻ የሚያገለግሉ አንዳንድ የመወያያ ርዕሶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

  • የሆነ ቀን ከእንክብካቤ በሚወጡበት ወቅት የግድ ሊኖሯቸው የሚገቡ ተጨባጭ ክህሎቶችን ለህጻናት ማስተማር የምንችለው እንዴት ነው? እንክብካቤ ካበቃ በኋላ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ክህሎቶች ምንድን ናቸው?
  • ዝም ብለው የተነገራቸውን ብቻ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲወሰኑ፣ የነገሮችን ጥቅም እና ጉዳት እንዲመዝኑ እና ኃላፊነት እንዲወስዱ ህጸናትን ለማስተማር የዕለት ተዕለት ውይይቶችን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

እባካችሁ በዕለት ተዕለት ሥራችሁ ውስጥ ማን ምን እንደሚሰራ የሚገልጽ የጊዜ ሰሌዳን ጨምሮ ዕቅዳችሁን ጻፉ።

ህጻናት እያደጉ ሲመጡ ከእንክብካቤ ለመውጣት የሚደረጉ ዝግጅቶች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ በሚደረጉ መደበኛ ስብሰባዎች እንዲሁም በኤስ ኦ ኤስ ሰራተኞች በሚመሩ የወጣቶች ቡድን ስብሰባዎች ሊቀጥሉ ይችላሉ።