Session 15/21

ገጽ 6/7 እንክብካቤ ካበቃ በኋላ የሚደረግ ማለማመድ (mentoring) እና ማህበረሰብ ውስጥ ማካተት

እንክብካቤ ካበቃ በኋላ የሚደረግ ማለማመድ (mentoring) እና ማህበረሰብ ውስጥ ማካተት

ከእንክብካቤ በኋላ በሚኖረው ህይወት ውስጥ ስኬታማ ለመሆን ከሁለት ምንጮች የሚገኝ አመራር እና አዲስ ማህበራዊ ትስስር ያስፈልጋል። አንደኛው ለረጅም ጊዜ እንደ አለማማጅ (mentor) የሚያገለግሉ አንድ ወይም ሁለት ልምድ ያላቸው የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር ሠራተኞችን መመደብ ነው። ሌላኛው የሚያስፈልገው ነገር ልምዶችን ለመለዋወጥ እና ብቸኝነትን ለመከላከል የሚያስችል በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ጥምረትን መፍጠር ነው። የሥራ ዕቅዳችሁ እነዚህን ሁለት ይዘቶች ያካተተ መሆን አለበት። የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ሠራተኞችን በማነጋገር እና ቢቻል በእንክብካቤ ውስጥ ካለፈው ወጣት ጋር በመጠያየቅ ሂደቱን መደገፍ ይችላሉ።
አለማማጅ (MENTOR) ማለት ቀድመው የነበሩትን ለወጣቱ በጣም ቅርብ የሆኑ ሰዎች የሚተካ ወሳኝ ሰው ነው

ከህጻንነት ጀምሮ እንክብካቤ ከሰጡን ሰዎች ጋር መለያየት ከባድ በመሆኑ ሊተካቸው የሚችል እና አስተማማኝ መሠረት እና ተጨባጭ አማካሪ ሆኖ የሚያገለግል አዲስ ሰው እንዲኖር ያስፈልጋል። እያንዳንዱ ወጣት ወይም አነስተኛ የወጣቶች ቡድን ከእንክብካቤ ከመውጣት አስቀድሞ በተገቢው ጊዜ አለማማጅ ሊመደብለት ይገባል። አንዳንዴ አንዲት የኤስ ኦ ኤስ እናት ጡረታ ልትወጣ እና የአደራ ቤተሰብ ወላጆች አዲስ ልጆችን በመንከባከብ ሊጠመዱ ይችላሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ የኤስ ኦ ኤስ ሠራተኞች ምድብ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አለማማጅ እንዲሆን ማንን መመደብ እንደሚችል ማወቅ ይኖርበታል።

እንክብካቤ ካበቃ በኋላ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ አስተማማኝ ቡድኖችን ማመቻቸት
መግቢያው ላይ እንደተማርነው በወጣትነት ወቅት ራስን መቻል ሊሳካ የሚቻለው እርስ በእርስ መደጋገፍ ያለበት አዲስ ማህበራዊ ትስስርን በመገንባት ብቻ ነው። ይህም ማለት ከማህበረሰቡ ጋር እንዲገናኝ፣ በአካባቢው ካሉ ቢዝነሶች ጋር ትውውቅ እንዲመሰርት፣ ከቤተሰቡ እና ከዘመዶቹ ጋር መልሶ እንዲገናኝ እና ከእኩዮቹ ጋር ትስስር እንዲኖረው ወጣቱን መርዳት አለብን ማለት ነው። ከእንክብካቤ በኋላ ከዕኩዮች ጋር ትስስር መመስረት ወጣቱ ወደ ማህበረሰቡ በሚመለስበት ወይም በሚገባበት ወቅት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ወጣቶች ከአለማማጃቸው (MENTOR)  ጋር መደበኛ በሆነ መልኩ በየጊዜው በቡድን በመገናኘት ስላጋጠሟቸው ተግዳሮቶች ሊወያዩ፣ ሥራ እና መኖሪያ ቤት ከመፈለግ፣ ከቤተሰብ እና ከትዳር ነክ ችግሮች እንደዲሁም ከሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተሞክሮአቸውን ሊለዋወጡ ይችላሉ። የቀድሞ የአደራ ቤተሰባቸውም እንዲሁ ምክር ሊሰጥ ይችላል።

 

በኬንያ በእንክብካቤ ውስጥ ያለፈች ወጣት የሆነችው ሩት እሷ እና ሌሎች በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች አንድ ላይ በመሆን የኬንያ በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ማህበር የተሰኘውን ጥምረት እንዴት እንደፈጠሩ ታስረዳለች። ማስፈንጠሪያውን ተከትላችሁ በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ሌሎች በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶችን ለመርዳት፣ ለመደገፍ እና አቅማቸውን ለማጎልበት የወሰዷቸው እርምጃዎች በመመልከት ራሳችሁን አነሳሱ።