ክፍለ ጊዜ 9/21

ገጽ 10/10 የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

“ሁሉም እንክብካቤ ሰጪ ትግበራቸው ያስገኘውን ውጤት ለማጋራት ጉጉት ነበራቸው (…)። ለምሳሌ አንዲት ፈጽሞ ፈገግ የማትል የነበረች ህጻን አንክብካቤ ሰጪዋ አስተማማኝ እንክብካቤ አሰጣጥን በእሷ ላይ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች ጀምሮ ፈገግ ማለት እንደጀመረች አጋርተዋል። በህጻኗ የመጠራጠር ባህሪ የተነሳ እንዴት ለህጻኗ ተደራሽ ከመሆን እና ትኩረት ከመስጠት ጎን ለጎን ቆፍጠን ያለ ባህሪ እንዳሳየቻት አጋርታለች።”

የአሰልጣኝ አስተያየት

ግንዛቤ የመገምገሚያ ነጥቦች

  • በህጻናት ላይ መተማመን የጎደለው የአቀራረብ ባህሪን የሚፈጥረው ምንድን ነው?
  • መሸሽ የሚታይበት የአቀራረብ ባህሪን መለየት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • መሸሽ የሚታይበት የአቀራረብ ባህሪ ላላቸው ህጻናት ሞያ የተላበሰ ባህሪ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ጥርጣሬ የሚታይበት የአቀራረብ ባህሪን መለየት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ጥርጣሬ የሚታይበት የአቀራረብ ባህሪ ላላቸው ህጻናት ሞያን የተላበሰ ባህሪ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ዝብርቅርቅ የአቀራረብ ባህሪን መለየት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ዝብርቅርቅ የአቀራረብ ባህሪ ላላቸው ህጻናት ሞያን የተላበሰ ባህሪ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?
  • አንድን ህጻን መተማመን ያለበት የአቀራረብ ባህሪን እንዲያዳብር ለመርዳት በጣም የተሻለ ዕድል የሚኖራችሁ በህይወቱ ውስጥ የትኛው ወቅት ላይ ነው?

“ሌሎች ህጻናት እና ዕቃዎች ላይ ካለማቋረጥ ጉዳት የሚያደርስ ልጅ ነበረኝ። በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተማርኳቸውን ዘዴዎች ስጠቀም ግን ትንሽ ተቀይሯል። አንዳንድ ጊዜ አሁንም እየፈተነኝ እንዳለ እና ስህተት እስክሰራ እየጠበቀኝ እንደሆነ ይሰማኛል።”

የሠራተኛ አስተያየት

ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚደረጉ ነገሮች
መልመጃ

እባካችሁ የሚከተሉትን ነገሮች አስቡ፡-

  • ልጃችሁ ምን ዓይነት ዘዴ ይታይበታል? ይህ በጣም ግልጽ የሚሆነው ከአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ ጋር ግንኙነት በሚጀምርበት ወቅት ወይም በዕለት ተዕለት ሁኔታ ውስጥ ህጻኑ ያለመተማመን፣ ከአቅሙ በላይ የሆነ ስሜት ወይም ፍርሀት ሲሰማው ነው።
  • ህጻኑ ያለመተማመን ባህሪ የሚያሳይባቸው የዕለት ተዕለት ሁኔታዎችን አስቡ። እንዴት የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪ በማሳየት ምላሽ እንደምትሰጡ አቅዱ፡-
  • ህጻኑ ሲገፋችሁ ወይም ሲወቅሳችሁ ተረጋጉ፣ ስሜቱን አገናዝቡ እንዲሁም ሩህሩህ ሁኑ።

ህጻኑ እገዛ እንደሚያስፈልገው ባያሳያችሁም እንኳን ለህጻኑ እገዛ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ስሜቶቻችሁን ግልጽ በሆነ መልኩ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

በርካታ የዕለት ተዕለት ግንኙነቶች ላይ ከሚከተሉት ውስጥ አንደኛውን ባህሪ የሚያሳይ በእናንተ እንክብከካቤ ስር ያለን አንድ ህጻን ግለጹ፡-

  • የመሸሽ
  • የመጠራጠር ወይም
  • የተዘበራረቀ ባህሪ

ህጻኑ ለሚያሳየው መተማመን የጎደለው ባህሪ እናንተ በምትሰጡት ምላሽ ላይ ተወያዩ። መተማመንን የሚፈጥር ባህሪ ማሳየት የሚከብደው መቼ ነው? ህጻኑ ሲተነኩሳችሁ ነው፣ ሲሸሻችሁ ነው፣ ሲጮህባችሁ ነው፣ ችላ ሲላችሁ ነው ወይስ ሌሎች ነገሮችን ሲያደርግ ነው?

ፍላጎት ስላሳያችሁ እያመሰገንን እስከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ድረስ ለምትሰሩት ሥራ መልካም ዕድል እንመኝላችኋለን!