ክፍለ ጊዜ 9/21
ገጽ 7/10 መተማመን የጎደለው የተዘበራረቀ የአቀራረብ ባህሪ
መተማመን የጎደለው የተዘበራረቀ የአቀራረብ ባህሪ
አንዳንድ ህጻናት ከእንክብካቤ ሰጪዎች ጋር በተያያዘ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት እና ፍርሀት ያሳለፉ ከመሆናቸው የተነሳ መሸሽ እና መጠራጠር ያለባቸው የአቀራረብ ዘዴዎቻቸው እንኳን መስራት ያቆማሉ። ይህ ሁኔታ ግራ የተጋባ ወይም የተዘበራረቀ ባህሪ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ለአጭር ጊዜ ሊከሰት ወይም በአንጻሩ ይበልጥ ቋሚ ሊሆን ይችላል። አንድ ህጻን ይህን ባህሪ በሚያሳይበት ወቅት በጣም ከመጨነቁ የተነሳ መቀራረብን እና መለያየትን ማስተናገድ የሚችልበት መንገድ አጥቷል ማለት ነው። ይህ ባህሪ አብዛኛውን ጊዜ የሚታየው ትንሽ ዕድሜ ላይ እያለ ህጻኑን ያነቃቃው ወይም የተንከባከበው ሰው ያልነበረ ከሆነ፤ ለምሳሌ እናትየው እራሷ ህጻን እያለች በጣም ችላ ተብላ የነበረች ወይም ህጻኑ ትንሽ እያለ ወላጆቹ ዕፅ በጣም ያለአግባብ ይጠቀሙ የነበሩ ወይም የጦርነት እና የቀውስ ተጠቂ ከነበሩ ነው።
ህጻኑ ወይም ታዳጊው፡-
- ምንም እንኳን እንክብካቤ ሰጪው አስተማማኝ ባህሪ የምታሳይ ቢሆንም እንክብካቤ ሰጪውን ሊፈራ ይችላል።
- ሁል ጊዜም ራሱን ዞር ሊያደርግ ይችላል፤ ለምሳሌ የእንክብካቤ ሰጪው ጭን ላይ በሚቀመጥበት ወቅት።
- እንክብካቤ ሲሰጠው የሚከተሉትን ግራ የሚያጋቡ ምላሾች ሊሰጥ ይችላል፡-
- ህጻኑ ወይም ልጁ እንክብከካቤ ሰጪዎቹ ወዳለበት ቦታ ሲገቡ በፍርሀት ደርቆ ሊቀር ይችላል፤
- ከእንክብካቤ ሰጪው ጎን ወዳለው ቦታ ሊመለከት እና አይኗን ሊሸሽ ይችላል፤
- መስተጋብር የማድረግ ምንም ፍላጎት ላይኖረው እና ደግሞ ደጋግሞ አንድ አይነት በሆነ መልኩ ሊጮህ፣ ተመሳሳይ ትርጉም የሌላቸውን ድምጾች ወይም ቃላት ሁል ጊዜ ደጋግሞ ሊያወጣ ይችላል፤
ወይም የእንክብካቤ ፍላጎቱን ድንገት የማወክ ሁኔታ ሊታይበት ይችላል፡- ከእናንተ ጋር መስተጋብር ሲጀምር እና ከእናንተ ጋር መስተጋብር ላይ እያለ ድንገት እንደ መጫወት ወይም ታግሏችሁ ለማሸነፍ እንደመሞከር ያለ ሌላ ነገር ማድረግ ሊጀምር ይችላል።
በዕድሜ ተለቅ ያለ ህጻን ወይም ታዳጊ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሊኖሩት ይችላሉ፡-
|
በአንዳንድ ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ ህጻኑ 5-7 ዓመት አካባቢ ዕድሜ ላይ “ሰውን ከመቅረብ ጋር የተያያዘ ችግር” ሊያጋጥመው ይችላል፡-
ህጻኑ ግልጽ በሆነ መልኩ ከሌሎች ሰዎች ጋር ማህበራዊ መስተጋብር ማድረግ ያቅተዋል እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ማህበራዊ ግንኙነቶችን መመስረት አይችልም። ይህ ግልጽ የሆነ ከሰው ጋር የመቀራረብ ዘዴ ያለመኖር ከባድ ችግር ነው እንዲሁም ይህ ባህሪ የሚታይባቸው ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ ሲያድጉ የሰብዕና ችገሮች (personality disorders) ያጋጥሟቸዋል (እንደ ስሜትን ያለመቆጣጠር/“Borderline”፣ ሰው የመጥላት ችግር/“Antisocial Personality Disorder”፣ ወዘተ ያሉ)።
የተዘበራረቀ ባህሪ ላለው ህጻን የሚሰጥ ሞያዊ እንክብካቤ
አንድ ህጻን ትንሽ ዕድሜ ላይ እያለ ከእንክብካቤ ሰጪዎች ጋር በነበሩት ግንኙነቶች ውስጥ የሚፈልጋቸውን ነገሮች በመነፈግ እና በዘፈቀደ በሚከሰቱ ለውጦች ውስጥ ያለፈ ከሆነ ሁሉም ነገሩ “ይዘገያል”። ትንሽ ዕድሜ ላይ የተከሰቱት በርካታ ችግሮች እና ጤናማ ያልሆነ እንክብካቤ የህጻኑ ዕድገት በተለይም ደግሞ ከማህበራዊ ዕድገት፣ ከስሜት ዕድገት እና ከአዕምሮ ዕድገት ጋር በተያያዘ እንዲንቀራፈፍ ያደርጋሉ።
በዚህም የተነሳ ህጻኑን ስታዩት በትልቅ ልጅ ሰውነት ውስጥ ያለ በጣም ትንሽ ልጅ ሆኖ ሊታያችሁ ይችላል፡-
|
- እንዲህ ዓይነት ባህሪ የሚያሳዩ በእንክብካቤ ስር ያሉ የምታውቋቸው ህጻናት አሉ?
- የተገለጹትን ባህሪዎች በሚያሳዩበት ወቅት በምን መልኩ ምላሽ ትሰጣላችሁ?
- በቤተሰባችሁ ውስጥ/ከጓደኞቻችሁ መካከል እንዲህ ዓይነት ባህሪ ሲያሳይ የነበረ የምታስታውሱት ሰው አለ?
- ህጻናት የመሸሽ ባህሪ በሚያሳዩበት ጊዜ ምላሽ ከመስጠት ጋር በተያያዘ በጣም የሚከብዳችሁ ነገር ምንድን ነው?