ክፍለ ጊዜ 9/21

ገጽ 5/10 መተማመን የጎደለው እና መሸሽ የሚታይበት የአቀራረብ ባህሪ

መተማመን የጎደለው እና መሸሽ የሚታይበት የአቀራረብ ባህሪ

አንድ ህጻን ወይም ታዳጊ ብዙም የማይገኙ፣ በጣም ብዙ ነገር የሚጠይቁ እና ለህጻኑ ብዙም ፍቅር የማያሳዩ እንክብካቤ ሰጪዎች የነበሩት ከሆነ እንክብካቤ ሰጪዎችን እና ቦታ የሚሰጣቸው ሌሎች ሰዎችን የመሸሽ ዘይቤን በማዳበር ምላሽ ሊሰጥ ይችላል። “የልጅ አዋቂ” ወይም “ራሱ ለራሱ ወላጅ” ለመሆን ሊሞክር ይችላል።

  • እንክብካቤ ሰጪው በሚሄድበት ወቅት ህጻኑ በማልቀስ ወይም በማዘን ምላሽ አይሰጥም።
  • በአሻንጉሊቶች ወይም በአንድ እንቅስቃሴ በጣም ይጠመዳል እንዲሁም እንክብካቤ ሰጪው ስትመለስ ከእሷ ጋር መስተጋብር አያደርግም። እንክብካቤዋን ችላ የማለት ሁኔታ ይኖረዋል።
  • በዕድሜ ተለቅ ያሉ ህጻናት እና ታዳጊዎች፡- በሚያስፈልጋቸው ጊዜም እንኳን እገዛ ወይም እንክብካቤ አይጠይቁም።
  • ስሜታቸውን ለመቆጣጠር ይሞክራሉ እንዲሁም ምን እንደሚሰማቸው በግልጽ አያሳዩም።
  • ከዕድሜአቸው በጣም ቀድመው ችግሮችን በራሳቸው ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ።
  • ከሰው ጋር እንደመለያየት እና ሰውን እንደማጣት ያሉ አሳዛኝ እና ከባድ ክስተቶችን ለማስታወስ እና ለመወያየት ይቸገራሉ።
  • ራሳቸውን ለመቻል ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ እንዲሁም ስሜቶችን ላለማሳየት እና ስለ ስሜቶች ላለማውራት ይታገላሉ።
  • አብዛኛውን ጊዜ ጨለምተኛ፣ የተጨነቁ፣ ስሜት የሌላቸው ይመስላሉ እንዲሁም እንደ “ምን አገባኝ?”፣ “አዋቂዎችን ማመን አያስፈልግም”፣ ወዘተ ያሉ ነገሮችን ይላሉ። “የብቸኝነት” ሁኔታ ውስጥ የመሆን አዝማሚያ አላቸው።

የመሸሽ ዘዴን የሚጠቀሙ ህጻናት ሰውን ማጣትን እና እንክብካቤ ማጣትን እንክብካቤ መፈለግ በማቆም ለመቋቋም የሚሞክሩ ከመሆኑም በላይ ከዚያ ይልቅ የመተማመን ስሜትን ለመፍጠር በሰዎች ፋንታ ነገሮችን (እንደ ቴዲ ቤር አሻንጉሊት ወይም አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ያሉ) በጣም ያቀርባሉ። እንዲያውም ግን የመሸሽ ባህሪ ያላቸው ህጻናት በጣም ጠንካራ የእንክብካቤ ፍላጎት አላቸው፤ ነገር ግን የመጀመሪያ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸውን ለማስደሰት አስቸጋሪ፣ ስሜት የሌላቸው እና የማይገኙ ስለነበሩ ህጻናቱ ፍላጎታቸውን ማፈንን ይማራሉ። ይህም ማለት አብዛኛውን ጊዜ በተሳሳተ መልኩ “ስሜት አልባ” ተደርገው ይታያሉ እንዲሁም የእንክብካቤ ሰጪን ትኩረት እና እገዛ የማይጠይቁ በመሆኑ በዕለት ተዕለት ሥራ ውስጥ ይረሳሉ ማለት ነው።

የመሸሽ ባህሪ ላላቸው ህጻናት ሞያዊ እንክብካቤ ማድረግ

የሚከተሉት የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪያት እንክብካቤን የሚሸሹ ህጻናትን በተመለከተ አስፈላጊ ከሆኑት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው፡-

  • በምትችሉበት ጊዜ ሁሉ ለህጻኑ እንክብካቤ ስጡ (ህጻኑ ባይጠይቅም እና ብቻውን መሆን ቢፈልግም እንኳን በራሳችሁ ተነሳሽነት እንክብካቤ ስጡት)።
  • ሁል ጊዜም የምትገኙ መሆናችሁን እና ትኩረት ለመስጠት እና ህጻኑን ለማዋራት ዝግጁ መሆናችሁን አሳዩ።
  • የራሳችሁን ስሜት ለመረዳት ቀላል በሆነ መልኩ ግለጹ እንዲሁም ህጻኑ እየተሰማው ነው ብላችሁ የምታስቡትን ነገር በራሳችሁ ቃላት “ተርጉሙ”። ለምሳሌ፡- “ወይኔ፣ መሬት ላይ ወደቅክ፤ በጣም የሚያም መሆን አለበት፤ እዚህ ጋር ናና ትንሽ ከእኔ ጋር ተቀመጥ”።
  •  እምቢ ቢልም ቀለል አድርጋችሁ “አይሆንም” በሉ፤ ህጻኑ የምታስፈልጉት ቢሆንም ፍላጎቱን ለማሳየት ስለሚፈራ ነው።  
  • በተዘዋዋሪ ማነጋገርን ተጠቀሙ፡- የመሸሽ ባህሪ ያለው ህጻን ስለ ግላዊ ነገሮች ማውራት በጣም ሊከብደው የሚችል ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ ዕቃዎች ይመስጡታል እንዲሁም በጣም ያቀርባቸዋል። ስለዚህ ለምሳሌ እንደ የህጻኑ ቴዲ ቤር አሻንጉሊት ወይም ስዕል ያለ መሳጭ ዕቃን ልትመለከቱ እና “ቴዲ ቤር አሻንጉሊቱ ስለሚሰማው ስሜት” ወይም አንድ ስዕል ውስጥ  ያሉ ቅርጾች እና ዕቃዎች እያደረጉ፣ እያሰቡ ወይም እየተሰማቸው ስላለው ነገር ህጻኑን ልታወሩት ትችላላችሁ። ያኔ ህጻኑ እናንተ በጠቀሳችኋቸው “ነገሮች አማካኝነት” ስለራሱ ያወራል።

መወያያ

  • እንዲህ ዓይነት ባህሪ የሚያሳዩ በእንክብካቤ ላይ ያሉ የምታውቋቸው ህጻናት አሉ?
  • እንክብካቤ ሰጪ እንዳያስብላቸው፣ ትኩረት እንዳይሰጣቸው እና እንዳያስተውላቸው በሚሸሹበት ወቅት በምን መልኩ ምላሽ ትሰጣላችሁ?
  • በቤተሰባችሁ ውስጥ/ከጓደኞቻችሁ መካከል እንዲህ ዓይነት ባህሪ ሲያሳይ የነበረ የምታስታውሱት ሰው አለ?
  • ህጻናት የመሸሽ ባህሪ በሚያሳዩበት ጊዜ ምላሽ ከመስጠት ጋር በተያያዘ በጣም የሚከብዳችሁ ነገር ምንድን ነው?