ክፍለ ጊዜ 9/21

ገጽ 8/10 የሞያዊ እንክብካቤ እና ሰውን በጣም የመቅረብ ጠቅላላ እይታ

የሞያዊ እንክብካቤ እና ሰውን በጣም የመቅረብ ጠቅላላ እይታ

በእንክብካቤ ስር ያሉ ህጻናት ጎጂ ወይም መተማመን የጎደላቸው የአቀራረብ አዝማሚያዎችን የማዳበር ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው። ከተፈጥሮ ወላጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጣሉ፣ አነስተኛ ዕድሜ ላይ እያሉ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው በርካታ ጊዜ ይቀያየራሉ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ በቀን ውስጥ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ብዙ ጊዜ ይቀያየራሉ። የአደራ ወይም የስጋ ዘመዶች ቤተሰብ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት አግባብ ያልሆነ አያያዝ ወይም የሚፈልጉትን ነገር መነፈግ ውስጥ ያልፋሉ።

(ስለ ህክምና ተጨማሪ ዕውቀት ለማግኘት እባካችሁ በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመውን እና ህክምናን የሚመለከተውን ይህን መጽሀፍ ተመልከቱ፡-

 www.attachment-disorder.net).

ለእነዚህ ህጻናት በእንክብካቤ ሥራችሁ ውስጥ ምን ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ እንዲሁም ምን ዓይነት ውጤቶችን መጠበቅ ትችላላችሁ?

ይህ ምን አልባት በአብዛኛው የሚወሰነው ህጻኑ ሞያዊ እንክብካቤ እንዲያገኝ የሚመደብበትን ዕድሜ መሠረት በማድረግ ሊሆን ይችላል። ህጻኑ እንክብካቤ እንዲያገኝ በሚመደብበት ወቅት ዕድሜው ከ20 ወራት በታች ከሆነ የአቀራረብ አዝማሚያውን ወደ ሞያዊ እንክብካቤ ሰጪው የአቀራረብ አዝማሚያ እንደሚቀይር በአደራ ቤተሰብ ልጆች ላይ የተሰሩ ጥናቶች ያሳያሉ፤ ሆኖም ግን ይህ ሰው ህጻኑ በማይተኛበት ሠዓት አብዛኛውን ጊዜ የሚንከባከበው ሰው መሆን አለባት።

ይህም ማለት አስተማማኝ እንክብካቤ አሰጣጥን ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ ህጻኑ ጤናማ በሆነ መልኩ ሰውን መቅረብን ሊማር ይችላል ማለት ነው።

እንክብካቤ ለመስጠት በምትቀበሏቸው ጊዜ በዕድሜ ተለቅ ያሉ ህጻናትን በተመለከተ ሰውን የመቅረብ ባህሪያቸው ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ ከባድ ስለሆነ ይበልጥ ትዕግስተኛ መሆን አለባችሁ፤ እንዲሁም ይህ ህጻን ህይወቱን በአግባቡ ለመምራት በተወሰነ መልኩ የእናንተ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ልትቀበሉ ይገባል (ተጨማሪ ዕውቀት ለማግኘት ከዴልዌር ዩኒቨርሲቲ ሜሪ ዶዚዬር ያሳተሟቸውን ጥቂት ሥራዎች ተመልከቱ፡- www.psych.udel.edu/people/detail/mary_dozier).