ክፍለ ጊዜ 9/21
ገጽ 2/10 ቅርርብ አዝማሚያን መለየት የሚቻልበት መንገድ – በሜሪ አይንስወርዝ የተዘጋጀ የሙከራ ዘዴ
የቅርርብ አዝማሚያን መለየት የሚቻልበት መንገድ – በሜሪ አይንስወርዝ የተዘጋጀ የሙከራ ዘዴ
ህጻናት በጣም አነስተኛ ዕድሜ ላይ እያሉ ከእንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ጋር ቅርበት ለመፍጠር አንዳንድ ዘዴዎችን ያዳብራሉ። እነዚህ ዘዴዎች የአቀራረብ አዝማሚያዎች ተብለው የሚጠሩ ሲሆን በሚከተሉት 4 ምድቦች ይመደባሉ፡- መተማመን ያለበት፣ የመሸሽ፣ ጥርጣሬ ያለበት እና የተዘበራረቀ። በዚህ ቪዲዮ ውስጥ ተመራማሪዎች በህጻናት እና በአዋቂዎች መካከል የሚደረጉ የተለያዩ መስተጋብሮችን እንዴት እንደሚያስተውሉ እና ህጻናቱ ከሰው ጋር በሚለያዩበት ጊዜ የሚያሳዩአቸው የተለያዩ ባህሪያት እንዴት ከእንክብካቤ ሰጪአቸው ጋር የፈጠሩት ቅርበት ምን ዓይነት እንደሆነ እንደሚያሳዩ ትመለከታላችሁ። በቪዲዮው ውስጥ የተሰጠው የመጀመሪያ ምሳሌ የመተማመን ስሜት ያለው ህጻን ከሰው ጋር ሲለያይ የሚያሳየውን ባህሪ የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ምሳሌ የመሸሽ ዘዴን የሚጠቀም ህጻንን የሚያሳይ ነው። ሦስተኛው ምሳሌ የመጠራጠር ዘዴን የሚጠቀም ህጻንን የሚያሳይ ነው። ከስነ-ምግባር ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የተነሳ በተዘበራረቀ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ህጻናትን የሚያሳዩ ቀረጻዎች የሉም።
ይህ ቪዲዮ johnbowlby.com የተሰኘው ድረገጽ ላይ ወይም ዩቲዩብ ላይ ይገኛል።