ክፍለ ጊዜ 9/21

ገጽ 3/10 የህጻናት መተማመን የጎደላቸው የአቀራረብ አዝማሚያዎች (የመሸሽ፣ የመጠራጠር፣ ወይም የተዘበራረቀ) እና እንክብካቤ ሰጪዎች የሚያሳዩት ባህሪ

የህጻናት መተማመን የጎደላቸው የአቀራረብ አዝማሚያዎች (የመሸሽ፣ የመጠራጠር፣ ወይም የተዘበራረቀ) እና እንክብካቤ ሰጪዎች የሚያሳዩት ባህሪ

ህጻናት የህይወታቸው የመጀመሪያ ዓመታት ላይ መተማመን ያለበት እንክብካቤ ውስጥ ካለፉ ምን ዓይነት ባህሪ ያሳያሉ የሚለውን በተመለከተ ክፍለ ጊዜ 6 ውስጥ ያልነውን ታስታውሳላችሁ፡-

  • እንክብካቤ ሰጪዎች አስተማማኝ መሠረት በሚሰጡበት ወቅት 0-2 ዓመት ዕድሜ ላይ ያለ ህጻን እንክብካቤ ሰጪው ስትሄድ ያለቅሳል (ነገር ግን ለረጅም ጊዜ አያለቅስም)። ብዙም ሳይቆይ ዳዴ ብሎ መሄድ እና ብዙ ጊዜ በመጫወት እና በማሰስ ማሳለፍ ይጀምራል።
  • በዕድሜ ተለቅ ያሉ ልጆች አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ ከመሆናቸውም በላይ ስለ ራሳቸው እና ስለ ሌሎች ሰዎች አዎንታዊ አመለካከት ይኖራቸዋል እንዲሁም እገዛ ሲያስፈልጋቸው ይጠይቃሉ። ከእኩዮቻቸው እና ከእንክብካቤ ሰጪዎች ጋር በርካታ የተለዩ ግንኙነቶች ይኖሯቸዋል።

ህጻናት ከመጀመሪያ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ጋር መተማመን የጎደለው ቅርበት እንደነበራቸው የሚጠቁሙ ሌሎች ሦስት የአቀራረብ አዝማሚያዎች አሉ።መተማመን የጎደላቸው የአቀራረብ አዝማሚያዎችን በምናጠናበት ወቅት እባካችሁ በእናንተ እንክብካቤ ስር ያሉትን ህጻናት አስቡ። ከገለጻው በኋላ በእናንተ እንክብካቤ ስር ያሉት ህጻናት ስትሄዱ ወይም ከእነሱ ጋር መስተጋብር ስታደርጉ ምላሽ ስለሚሰጡበት መንገድ ትወያያላችሁ።