ክፍለ ጊዜ 9/21
ገጽ 4/10 ሦስቱ መተማመን የጎደላቸው የአቀራረብ ባህሪያትሦስቱ መተማመን የጎደላቸው የአቀራረብ ባህሪያት
እነዚህ የአቀራረብ ዘዴ ዓይነቶች እያንዳንዳቸው ከሞላ ጎደል ጠንከር ባለ መልኩ ሊገለጹ የሚችሉ ናቸው። ስለሆነም ልጃችሁ የተወሰኑ ባህሪዎችን ብቻ ሊያሳይ የሚችልበት ዕድል አለ።
በርካታ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች (የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪያትን ተግባራዊ ቢያደርጉም እንኳን) መገፋት እና ንዴት ያጋጥማቸዋል። ይህ በሚከሰትበት ወቅት በህጻኑ ውስጥ የሚፈጠረውን ነገር የሚያሳየው የቦውልቢ ንድፈ ሀሳብ በጣም ይጠቅማል። ህጻኑ ትንሽ ዕድሜ ላይ እያለ ከአዋቂዎች ጋር በነበሩት ግንኙነቶች ማህበራዊ ባህሪውን የሚቆጣጠረውን መስተጋብር መሠረት በማድረግ ምን መጠበቅ እንዳለበት የሚጠቁሙ ስሜቶችን ያዳብራል። ህጻኑ እናንተ መልካም የሆነ እና ርህራሄ የተሞላበት እንክብካቤ ልትሰጡት ለምታደርጉት ጥረት ተገቢውን ምላሽ ላይሰጥ ይችላል ምክንያቱም ትንሽ ዕድሜ ላይ እያለ ለምሳሌ ከክህደት፣ አግባብ ካልሆነ አያያዝ፣ ከቁርጠኝነት ማነስ፣ ወዘተ ጋር የተያያዙ አሉታዊ ተሞክሮዎችን ያሳለፈ በመሆኑ አንዳንድ አሉታዊ ነገሮችን ሊጠብቅ ይችላል።
ምሳሌው የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪን ተግባራዊ የሚያደርግ ቢሆንም ህጻኑ ከዚያ ቀደም ያሳለፈውን እና የህጻኑን የውስጥ አስተሳሰብ የቀረውን መተማመን የጎደለው ተሞክሮ የሚጋፈጥ አንድ እንክብካቤ ሰጪን የሚያሳይ ነው። በህጻኑ ውስጥ ይበልጥ አዎንታዊ የሆነ የውስጥ አስተሳሰብን ለመገንባት ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ነገር ግን በአደራ እንክብካቤ ግንኙነቱ ውስጥ አዎንታዊ ተሞክሮዎችን በመደጋገም ሊሳካ ይችላል።