ክፍለ ጊዜ 9/21
ገጽ 1/10 መተማመን የጎደለው የአቀራረብ ባህሪን መገንዘብ እና ማሻሻል የሚቻልበት መንገድመተማመን የጎደለው የአቀራረብ ባህሪን መገንዘብ እና ማሻሻል የሚቻልበት መንገድ
ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-
- መተማመን የጎደለው የአቀራረብ ባህሪን በህጻናት ላይ መለየት።
- ጥርጣሬ ያለበት የአቀራረብ ባህሪን በህጻናት ላይ መለየት።
- መተማመን የጎደለው የተዘበራረቀ የአቀራረብ ባህሪን በህጻናት ላይ መለየት።
- እነዚህን ሦስት የአቀራረብ ባህሪያት ባለሞያነትን በተላበሰ መልኩ እንዴት ማስተናገድ እና ህጻናት መተማመን እንዲሰማቸው ማድረግ እንደምንችል ማወቅ።
የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-
በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ በትንሽ ዕድሜ የሚከሰቱ ሰውን ከመቅረብ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውን የሚጠቁሙ ምልክቶችን እንዴት ማስተዋል እና መለየት እንደምትችሉ (ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት አንዳንድ ጊዜ መተማመን የጎደለው የአቀራረብ ባህሪን እንዴት እንደሚያዳብሩ) ትለማመዳላችሁ።
መተማመን የጎደለው የአቀራረብ ባህሪ ካላቸው ህጻናት ጋር በተያያዘ እንዴት ሥራችሁን መሥራት እንዳለባችሁ ምክሮችን ታገኛላችሁ።
የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-
የቤተሰብ መልክ በሌለው እንክብካቤ ውስጥ የሚመደቡ የወላጆቻቸውን እንክብካቤ ያጡ ህጻናት እና ልጆች አብዛኛውን ጊዜ በትንሽነት ዕድሜያቸው ብዙ ችግሮችን ያሳለፉ ናቸው፡- ምን አልባት ከጊዜያቸው ቀድመው መወለድ እና ዝቅተኛ ክብደት ይዘው መወለድ (ይህም በዕድገታቸው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል)፣ በህይወታቸው ውስጥ ችግር ያለባቸው ወላጆች የነበሯቸው በመሆኑ አስተማማኝ እንክብካቤ ያለማግኘት፣ እና የእንክብካቤ ሰጪዎች በተደጋጋሚ መቀያየር።