የስልጠና ክፍለጊዜ 17/21

ገጽ 2/9 መግቢያ፡- የማገገሚያ ሠራተኞች እና የወደፊት የአደራ ወላጆችች በጋራ መሥራት የሚችሉበት መንገድ

መግቢያ፡- የማገገሚያ ሠራተኞች እና የወደፊት የአደራ ወላጆችች በጋራ መሥራት የሚችሉበት መንገድ

ጫናን በሚፈጥሩ በርካታ ምክንያቶች የተነሳ ጎዳና ላይ ለመኖር የሚገደዱ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ በማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ሠራተኞች እና የአደራ ወላጆች ለነዚህ ህጻናት በቂ እንክብካቤ መስጠት መቻል ይኖርባቸዋል። አብዛኛዎቹ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት አሰቃቂ ተሞክሮዎች ያሏቸው በመሆኑ እና ፍቅር እና እንክብካቤ ይሰጡናል ብለው አዋቂዎችን ማመን ያቆሙ በመሆናቸው ይህ ሥራ አብዛኛውን ጊዜ ፈታኝ ነው። በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በቀድሞ ህይወታቸው የጎዳና ተዳዳሪ የነበሩ ህጻናትን ለመረዳት፣ ለመለየት እና እምነታቸውን ለማግኘት የሚያስችል የስሜት መነቃቃት እና ተጨባጭ መገልገያዎችን ታገኛላችሁ። አንዳንድ ህጻናት ከዘመዶቻቸው ጋር መልሰው መገናኘት የሚችሉ ቢሆንም ይህ ክፍለ ጊዜ የሚያተኩረው ከዘመድ ጋር ምንም ግንኙነት ከሌላቸው እና ቤተሰብ እንዲመደብላቸው ከሚያስፈልጋቸው ህጻናት ጋር በተያያዘ በሚሠራ ሥራ ላይ ይሆናል። የመልሶ ማገገሚያ ሠራተኞች እና የአደራ ወላጆች በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ አብረው እንዲሳተፉ እና ተጋግዘው እንዲሰሩ እንመክራለን።

በጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት መልሶ የማገገመም እና የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ዙሪያ በአፍሪካ ከተሰሩ ምርምሮች የተገኙ ዕውቀቶችን ትማራላችሁ። እያንዳንዱ ደረጃ ላይ በጋራ እንድትወያዩ እና እንድታቅዱ ሀሳቦችን እናቀርባለን።

በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ስለ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ያሏችሁን የግል ተሞክሮዎች እና ዕውቀቶቻችሁን እንድታካፍሉ፤ ዕውቀታችሁን ከሌሎች ሰዎች ጋር እንድትለዋወጡ እንዲሁም እንድትወያዩ በትህትና እንጠይቃለን። ክፍለ ጊዜው በየአካባቢው ያሏችሁን የየራሳችሁን አሠራሮች ይበልጥ እንድታሻሽሉ የሚያነሳሳ የጋራ መድረክ ነው።