ክፍለ ጊዜ 17/21

ገጽ 5/9 የተለያዩ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምድቦች የሚያስፈልጓቸው የተለያዩ ፕሮግራሞች ናቸው

የተለያዩ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምድቦች የሚያስፈልጓቸው የተለያዩ ፕሮግራሞች ናቸው

ሁሉም የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ተመሳሳይ የአገልግሎት ፕሮግራሞች አያስፈልጓቸውም። የአንድ የምስራቅ አፍሪካ ጥናት ግኝት ሁለት የተለያዩ ምድቦች እንዳሉ ያሳያል። አንደኛው የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምድብ ከቤተሰባቸው ጋር መልሶ ሊቀጥል የሚችል ዓይነት ግንኙነት ያላቸው ህጻናትን በውስጡ የያዘ ሲሆን ሁለተኛው ምድብ ደግሞ በተጨባጭ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ህጻናትን በውስጡ የያዘ ነው።

  1. ከአሥር የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ውስጥ ከሰባት የሚበልጡት ማታ ማታ የሚሆኑት እቤት ነው እንዲሁም ጎዳና ላይ የሚሆኑት ቀን ላይ ብቻ ነው። እነዚህ ህጻናት “ጎዳና የወጡ ህጻናት” ተብለው ይጠራሉ። ወደ ጎዳና የሚመጡት ከእኩዮቻቸው ጋር ጊዜ ለማሳለፍ፤ ምናልባትም ምግብ ለማግኘት ወይም ወላጆቻቸው ችግር ውስጥ ስለሆኑ ሊሆን ይችላል። በዚህ ምድብ ውስጥ በድህነት የተነሳ በቋሚነት ጎዳና ላይ የሚኖሩ ወላጆች ያሏቸው ልጆችንም እንዲሁ ታገኛላችሁ።

እነዚህ ህጻናት አሁንም ከቤተሰባቸው ጋር ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ መልሰው እንዲያገግሙ የሚሰራው ሥራ አብዛኛውን ጊዜ የሚያተኩረው ከወላጆቻቸው ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር በመነጋገር ከቤተሰባቸው ጋር መልሰው እንዲቀላቀሉ በማድረግ ላይ ነው። ከእነዚህ ህጻናት ውስጥ አንዳንዶቹን በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ከዘመዶቻቸው ጋር መልሶ መቀላቀል የማይቻል ሊሆን ይችላል። እንደዚያ ከሆነ በሚቀጥለው ምድብ ውስጥ ይካተታሉ።

2. ሁለተኛው ምድብ በአንጻሩ በጣም አነስተኛ እና ምናልባትም ከአሥር ህጻናት ውስጥ ሦስቱን የሚይዝ ነው። እነዚህ ህጻናት “ጎዳና ቤታቸው የሆነ ህጻናት” ይባላሉ። በህይወታቸው ውስጥ ከወላጆቻቸው ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም (ቀንም ሆነ ሌሊት ብቸኛው ቤታቸው ጎዳና ነው)። እንክብካቤ እና ጥበቃ ለማግኘት የሚሞክሩት በጎዳና ላይ ከሚያውቋቸው ሰዎች ነው።

በዚህ ሁለተኛ ምድብ ውስጥ ያሉ ህጻናት እንዲያውም የወላጅ እንክብካቤ ያጡ እና በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ የሚያስፈልጓቸው ወይም ምናልባትም በኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደር ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።

በአካባቢያችሁ ባለው ማህበረሰብ ውስጥ መልሶ ማገገም በጣም የሚያስፈልጋቸው እነማን እንደሆኑ ለመለየት የሚከተለውን ውይይት አድርጉ፡-

የቡድን ውይይት

15 ደቂቃ
በአካባቢያችን ያሉ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት – ማን ላይ ነው ሥራ መሥራት ያለብን?

  • ቀን ቀን ብቻ ጎዳና ላይ የሚሆኑ እና ማታ ላይ ቤተሰባቸው ጋር ተመልሰው የሚሄዱ የምታውቋቸው የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት አሉ? ወይም ደግሞ ጎዳና ላይ የሚኖሩ ወላጆች ያሏቸው?
  • ከቤተሰብ እና ከዘመድ ጋር መልሶ የማቀላቀል ፕሮግራሞች አሏችሁ?
  • ምንም ዓይነት የቤተሰብ ግንኙነት ከሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ትሰራላችሁ?
  • በጣም ወሳኝ የምትሏቸው ተሞክሮዎቻችሁ ምንድን ናቸው?

እባካችሁ የሚከተለውን ማስታወሻ ያዙ፡- በማህበረሰባችሁ ውስጥ በተጨባጭ የወላጅ እንክብካቤ ያጡት የትኞቹ ህጻናት ናቸው?