ክፍለ ጊዜ 17/21

ገጽ 7/9 ከመልሶ ማገገሚያ ማዕከሉ የአደራ ቤተሰብ ማቅረብ

ከመልሶ ማገገሚያ ማዕከሉ የአደራ ቤተሰብ ማቅረብ

ከዚህ በአካባቢያችሁ ያሉ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናትን የግንኙነት መረብ የመለየት ሂደት በመነሳት ሠራተኞች እና የወደፊት የአደራ ወላጆች በማገገሚያ መዕከሉ የሚገኙትን ህጻናት ሊያስተውሉ እና እነማን ከአደራ ቤተሰቦች ጋር መጣመር እንዳለባቸው ሊስማሙ ይችላሉ። የወደፊት የአደራ ወላጆች የማገገሚያ ማዕከሉን መደበኛ በሆነ መልኩ በመጎብኘት ከህጻናቱ ወይም በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ልጆች ጋር ኢ-መደበኛ በሆነ መልኩ መገናኘት፣ በዕለት ተዕለት እንቅስቀሴዎች ውስጥ መሳተፍ እና ማን ቤተሰብ እንደሚያስፈልገው ከሠራተኞች ጋር በመሆን መወሰን አለባቸው።

አንዳንዶቹ የአደራ ወላጆች አስቀድመው የሚንከባከቧቸው ህጻናት ያሏቸው ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ አዲስ ሊሆኑ ይችላሉ። የሚከተለው ለእነሱ የቀረበ የመጀመሪያ ገለጻ ነው።

ህጻኑን/ኗን ከአደራ ቤተሰብ ጋር ማስተዋወቅ
አሁን ደግሞ ህጻኑን/ኗን የምናነጋግርበት እና የአደራ ቤተሰብ የምናቀርብበት ጊዜ ነው። አንድ ሠራተኛ እና አንድ የአደራ አሳዳጊ ይህን አብረው ሊያደርጉ ይችላሉ። ስለ ሁኔታው ህጻኑን/ኗን አነጋግሩ። በጣም የሚወደው/የምትወደው ምን እንደሆነ፣ ስለምን እንደሚያልም/እንደምታልም ወይም ምን እንደሚፈልግ/እንደምትፈልግ ተወያዩ። የማወቅ ጉጉት ይኑራችሁ እንዲሁም ከትዝብት ነጻ ሁኑ። በጥንቃቄ አዳምጡ እንዲሁም የሚነግራችሁን/የምትነግራችሁን ማንኛውንም ነገር ተቀበሉ። ልክ ነው ልክ አይደለም ብላችሁ አትተቹ፤ ፍቅር አሳዩ። ምን አልባትም እያናገራችኋቸው እያለ ከእነሱ ጋር ማድረግ የምትችሉት አነስተኛ እንቅስቃሴ ብታስቡ ጥሩ ነው። ልታስቋቸው ወይም ፈገግ ልታሰኟቸው ከቻላችሁ ግማሽ መንገድ እንደሄዳችሁ ይቆጠራል። የሆነ ጨዋታ ወይም እንቆቅልሽ ብትጫወቱ ወይም አብራችሁ ምግብ ብታዘጋጁ ጥሩ ነው።

የጎዳና ህይወት ለህጻናት እንዴት ከባድ እንደሆነ እና በርካታ ህጻናት ወላጆቻቸውን ወይም ዘመዶቻቸውን ያጡ ወይም ትተው የመጡ እንደሆኑ አብራሩ። ምን ማቅረብ እንደምትችሉ ግለጹ። የአደራ አሳዳጊዎች የህጻኑ ወላጆች እንዳልሆኑ ለህጻኑ/ኗ አስረዱ። ነገር ግን ህጻኑ/ኗ እስከሚያድግ/እስከምታድግ ድረስ ፍቅር፣ ምግብ፣ ጥበቃ እና ትምህርት እንደሚሰጡት/ጧት አስረዱ። በተጨማሪም የጎዳና ጓደኞቹ/ቿ ከናፈቁት/ቋት ወደ ጎዳና ወይም በአደራ ቤቱ ውስጥ እንዲጠያየቁ ሊመቻችላቸው እንደሚችል ለህጻኑ/ኗ ንገሩ። ይህም መጥፋት እንደማይኖርበት ለህጻኑ ያሳውቀዋል። አንዲት ልጅ ሁለት ጊዜ ጠፍታ እንደሄደች እና በመጨረሻም ከአንድ ዓመት በኋላ ከአደራ አሳዳጊዎቿ ጋር ለመኖር እንደወሰነች ሁለት የአደራ አሳዳጊዎች ነግረውናል። አንድ ህጻን ምንም ያህል ድሀ ቢሆን ማህበራዊ ትስስሩን ለመተው ምን ያህል እንደሚከብደው መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ህጻኑ ከመወሰኑ በፊት የአደራ ቤተሰሰቡን እንዲጎበኝ አድርጉ እንዲሁም ከመጨረሻው ውሳኔ አስቀድማችሁ የሙከራ ጊዜ ስጡት። የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት በህይወት ውስጥ የራሳቸውን ውሳኔ (በተለምዶ ወላጆች ብቻ የሚወስኗቸውን ዓይነት ውሳኔዎች) የሚወስኑ የልጅ አዋቂዎች መሆናቸውን አስታውሱ። በዚህ ሂደት ውስጥ መረጃ በሚገባ የማግኘት እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አካል የመሆን መብት አላቸው።

ህጻኑ እና የአደራ ወላጆቹ የሚጣጣሙ መሆናቸውን መገምገም

ህጻኑን ከማነጋገራቸው በፊት እና በኋላ ሠራተኞች እና የአደራ ወላጆች ህጻኑ እና የአደራ ወላጆቹ የሚጣጣሙ ስለመሆኑ መወያየት ይችላሉ። መተማመን በጎደለው መልኩ ሰውን የመቅረብ ባህርይ ያላቸው ህጻናት 3-5 ዓመት ሳይሞላቸው በፊት የአደራ ቤተሰብ ውስጥ ከገቡ ካሳለፉት አሰቃቂ ተሞክሮ የማገገም እና መተማመን በተሞላበት መልኩ ሰውን የመቅረብ ከፍተኛ ዕድል እንደሚኖራቸው ሁሉም ሰው ሊያውቀው ይገባል። በዕድሜ ተለቅ ያሉ ወይም በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆችን በተመለከተ የአደራ ወላጆች በዕድሜ ተለቅ ያሉ ልጆች በአንጻሩ ቋሚ የሆኑ ተግዳሮቶች ሊኖሩባቸው እንደሚችል እና በእንክብካቤ ላይ እያሉ ተጨማሪ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ሊያውቁ ይገባል። በተለይም ደግሞ የመጠራጠር ባህርይ የሚታይባቸው ህጻናት በአደራ ቤተሰብ ውስጥ ለማሳደግ አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ። የአደራ ወላጆች ልምድ ባለው ሠራተኛ ወይም የስነ-ልቦና ባለመሞያ መደበኛ ቁጥጥር እንዲደረግባቸው እንመክራለን።