ክፍለ ጊዜ 17/21

ገጽ 4/9 የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት እንክብካቤ ስናቀርብላቸው ምን አይነት ምላሽ ይሰጣሉ?

የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት እንክብካቤ ስናቀርብላቸው ምን አይነት ምላሽ ይሰጣሉ?

የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት “የህጻን አዋቂዎች” ናቸው

የጎዳና ህጻናት ከማገገሚያ ሠራተኞች ወይም ከአደራ ቤተሰቦች ለሚያገኙት እንክብካቤ የሚሰጡት ምላሽ በፍቅር እና በእንክብካቤ ያደጉ ህጻናት ከሚሰጡት ምላሽ በጣም የተለየ ነው። ፍቅር ያገኙ ህጻናት የሚየስቡት እንደሚወዷችሁ እና እንደሚያምኗችሁ ነው። የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ደግሞ የሚያስቡት እናንተን ማነጋገር ለሚቀጥለው አንድ ሠዓት በህይወት ለመቆየት እንደሚረዳቸው (ምግብ፣ ገንዘብ፣ የቅርብ ጊዜ ጥበቃ ሊሰጠኝ/ልትሰጠኝ ይችላል/ትችላለች ወይስ አይችልም/ አትችልም?) የሚለውን ነው። በአንጻሩ በጣም የበለጠ ጭንቀት አለባቸው እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ በሰው ላይ መሰረታዊ እምነት የላቸውም። ወዲያውኑ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሊያሟሉላቸው በሚችሉ ሰዎች መካከል ቶሎ ቶሎ እዚህ እዚያ ይላሉ።

ወላጆችን ጥሎ መሄድ ወይም ማጣት እና ጎዳና ላይ መኖር አብዛኛውን ጊዜ አሰቃቂ ህይወት ያሳለፉ ህጻናት ወይም በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆች በራሳቸው ለመኖር በሚያስችል መልኩ ከመብሰላቸው እና ዝግጁ ከመሆናቸው ረጅም ጊዜ አስቀድመው የሚወስኑት የጭንቅ ውሳኔ ነው። ከዚህም አንጻር በወላጅ ወይም በአዋቂ እንክብካቤ ማግኘትን ማመን ያቆሙ እና ለህይወታቸው ኃላፊነት መውሰድ የኖረባቸው “የልጅ አዋቂዎች” ይሆናሉ። እንክብካቤ ከማጣት ጋር በተያያዘ ያሳለፉት አሰቃቂ ሁኔታዎች በመኖራቸው የተነሳ አብዛኛውን ጊዜ የመልሶ ማገገሚያ ሠራተኞችን የመጠራጠር ሁኔታ ይታይባቸዋል ወይም ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ከአደራ ቤተሰባቸው ወጥተው ይጠፋሉ። የመጀመሪያዎቹ በርካታ ግንኙነቶች ላይ ህጻናቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሰጡት ምላሽ ያለመፈለግ ወይም የንዴት ነው። የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት በአዋቂ እንክብካቤ እና አመራር ላይ ያላቸውን እምነት መልሶ መገንባት ምን ያህል ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ልትገነዘቡ ይገባል።

ህጻናት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኟቸው የሚያሳዩት የመተማመን ስሜት የጎደለው አቀራረብ
አስተማማኝ ፍቅር እና እንክብካቤ አግኝተው ያደጉ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ስታገኟቸው የመቆጠብ ሁኔታ ሊያሳዩ ይችላሉ፤ ነገር ግን መልካም ዓላማ እንዳላችሁ ካሳመናችኋቸው ብዙም ሳይቆዩ እናንተን ማመን ይጀምራሉ እንዲሁም ለእናንተ የቅርበት ስሜት ይሰማቸዋል (ሠራተኞች እና እንክብካቤ ሰጪዎች የወላጅ ምትክ ሊሆኑ ይችላሉ)። ለምሳሌ የአሥር አመቱ ቢሳንግዋ ከወላጆቹ ጋር በፍቅር ካደገ በኋላ ነበር ወላጆቹ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው። ለመኖር ሲል ወደ ጎዳና ወጣ። በመልሶ ማገገሚያ ማዕከሉ ውስጥ በሚሰጠው ነገር ደስተኛ ነው። ከአደራ ቤተሰብ ጋር እንዲተዋወቅ ሲደረግ ብዙም ሳይቆይ ለእነሱ የቅርበት ስሜት ተሰምቶታል፤ እንዲሁም አሁን በጥሩ የአስተዳደግ ሁኔታ ላይ ይገኛል።

ከኃይለኛ፣ ከሱሰኛ ወይም ከቸልተኛ ወላጆች ጋር ካደጉ ህጻናት ወይም ወላጆቻቸው ከተዋቸው ህጻናት ጋር ቅርርብ ለመመስረት ግን በጣም ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል። እንዲህ ያሉት ህጻናት እንክብካቤ የማግኘት ፍላጎት ቢኖራቸውም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ የሚሰጧችሁ ምላሽ ከሚከተሉት አንደኛውን የመተማመን ስሜት የጎደለው ባህርይ የሚያንጸባርቅ ነው፡-

  1.  የመተማመን ስሜት የጎደለው የመሸሽ ባህርይ፡- ዲዶ ሰባት ዓመቱ ነው። ከእናንተ ምንም እርዳታ አይጠብቅም እንዲሁም ምንም ስሜት አያሳይም። ከሞላ ጎደል ፈጽሞ ፈገግ አይልም ወይም አያለቅስም፤ ፊቱ “ድንጋይ” ነው። ራሱን የቻለ “የህጻን አዋቂ” ለመሆን ይሞክራል፤ የምታቀርቡለትን ነገሮችም የሚያየው እንደ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት ነው። ለእናንተ እንዴት ፍላጎቶቹን እና ስሜቶቹን መግለጽ እንደሚችል አያውቅም። አብዛኛውን ጊዜ ደስተኛ ከመሆን እና ካለው ሁኔታ ጋር አብሮ ከመሄድ ይልቅ የጭንቀት እና የመቁነጥነጥ ስሜት ውስጥ ነው። በውስጡ ፍቅር እና እንክብካቤን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ፍላጎቶቹን እንዴት መግለጽ እንደሚችል አልተማረም። በመልሶ ማገገም ላይ እያለ የአደራ እናት ከምትሆነው ከሮቤርታ ጋር ለመኖር ተስማማ። ስሜቶቹን እና ሀሳቦቹን እንዲገልጽ ትረዳዋለች እንዲሁም መጠየቅ በማይችልበት ጊዜም እንኳን በራሷ ታቅፈዋለች እና እንክብካቤ ታደርግለታለች። ከአንድ ዓመት በኋላ እሷን ሊያምናት ችሏል። አሁን በጣም የበለጠ ደስተኛ እና በሁኔታዎች የሚደሰት ሰው የሆነ ይመስላል።

2. የመተማመን ስሜት የጎደለው እና የመጠራጠር ባህርይ፡- ሮበርት ዕድሜው 12 ዓመት ነው፤ ያደገውም በጣም ለመገመት አስቸጋሪ ከሆኑ ወላጆች ጋር ነው። አባቱ አንዳንድ ጊዜ ፍቅር የሚያሳይ ነበር፤ እንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከመጠን ይናደድ ነበር። እናቱ የአእምሮ ህመም የነበረባት በመሆኑ እንክብካቤ የምታደርግለት አንዳንድ ጊዜ መለስ ሲያደርጋት ነበር። የሮበርት ፍቅር የማግኘት ፍላጎት ለእንክብካቤ ሰጪዎች ካለው መሠረታዊ ፍርሀት ጋር የተቀላቀለ በመሆኑ በመልሶ ማገገሚያ ውስጥ ላሉ ሠራተኞች የሚያሳየው ባህርይ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። ኤሪክ የተባለውን ሠራተኛ ይወደዋል፤ ሴቶቹን ሠራተኞች ግን ሁል ጊዜም ይተቻቸዋል እንዲሁም ያላግጥባቸዋል። ቅርበትን እና እንክብካቤን ይፈልጋል፤ ግን ደግሞ በጣም ይፈራችኋል። ሠራተኞች ርህራሄ ሲያሳዩትም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ ይወቅሳቸዋል፣ በጣም ይጠራጠራቸዋል፣ ሀይለኛ ሊሆንባቸው እና ሊቆጣጠራቸው ይሞክራል እንዲሁም ሌሎች ህጻናትን ያሰቃያል። አንዴ ማንም ሰው አይወደኝም ብሎ ያማርራል፤ ከዚያ ደግሞ አልወደዳችሁኝም ብሎ ፊት ይነሳችኋል እንዲሁም ይወቅሳችኋል። ግጭቶች ከተፈጠሩ በኋላ ብዙ ጊዜ ጠፍቶ ይሄዳል፤ ግን ሁል ጊዜም ተመልሶ ይመጣል። ከዚያም ልምድ ያለው፣ የተረጋጋ እንዲሁም ግልጽ ገደቦችን እና የስነ-ምግባር ሕጎችን የሚያስቀምጥ የአደራ አባት ያለበት የአደራ ቤተሰብ ውስጥ ተመደበ። ከአንድ ዓመት በኋላ ትምህርት ቤት ገብቶ ብዙም ግጭቶች ውስጥ ሳይገባ ከጓደኞቹ ጋር መጫወት የሚችልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል፤ ነገር ግን በቅርብ ግንኙነቶች ውስጥ አሁንም በጣም በቀላሉ ለመጎዳት ቅርብ ነው።

3.የመተማመን ስሜት የጎደለው የተዘበራረቀ ባህርይ፡-
አውሮር ዕድሜዋ አምስት ዓመት ነው፤ በ12 ዓመት ዕድሜዋ በልጅነት የወለደቻት ደሀ እናቷ ከተወለደች ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ችላ ብላታለች። ጎዳና ላይ ስትገኝ የምግብ እጥረት ነበረባት። መልሶ ማገገሚያ ማዕከሉ ውስጥ ሁሉንም ሰው ታነጋግራለች እንዲሁም በጣም ደስ በሚል እና ልጃ ልጅ በሆነ መንገድ ትኩረታቸውን ለማግኘት ትሞክራለች። የማንኛውም ሠራተኛ እና በእንግድነት የመጣ ማንኛውም የማታውቀው ሰውም ጭምር ጭን ላይ መቀመጥ ትፈልጋለች። ነገር ግን የምታደርጋቸው ግንኙነቶች በጣም አጭር እና የዘፈቀደ በመሆናቸው ከየትኛውም ሠራተኛ ጋር ጥልቅ ግንኙነት ወደ መመሥረት አያመሩም። ከደቂቃ በፊት የተፈጠረውን ነገር አታስታውስም። ከእንክብካቤ ሰጪ ጋር የመቀራረብ ችሎታዋ የመጀመሪያው ዓመት ላይ አልዳበረም። ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወት ብትችልም ለአፍታ ያህል ብቻ ነው፤ እንዲሁም በጣም በቀላሉ ትኩረቷ ይሰረቃል። ለአንድ ዓመት ያህል የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ከቆየች በኋላ ከአደራ ወላጆቿ ብቻ እንክብካቤ እና ጥበቃ ለማግኘት መፈለግ ጀምራለች፤ ትንሽ ፍቅር ታሳያቸውም ጀምራለች።

1. Insecure avoidant behaviour: Dido is seven years old. He does not expect any help from you, and shows no feelings. He almost never smiles or cries, he has a “stone face”. He tries to be an independent “little grown-up”, and he sees your offers as an unwelcome interference. He does not know how to show his needs and feelings towards you. He is more often tense and restless, than happy and spontaneous. Deep inside, he wants love and care, but he never learned how to show his needs. In rehabilitation, he accepts living with foster mother Roberta. She helps him express his feelings and thoughts, and actively provides hugs and care even when he is not able to ask for it. One year later he is devoted to her. Now he looks much happier and more spontaneous.

2. Insecure ambivalent behaviour: 12-year-old Robert grew up with very unpredictable parents. His father was sometimes loving, and sometimes had fits of rage. His mother was mentally ill, and only cared for him when she sometimes was well. Because Robert’s need for love is mixed with a basic fear of caregivers, he acts in a very confusing way towards staff in the rehabilitation centre. He adores staff member Eric, but always criticizes and mocks female staff. He longs for intimacy and care, but at the same time he’s very afraid of you. Even when staff act kindly, he will often blame them, be very suspicious, try to dominate or control them, and bully other children. One minute he complains that nobody likes him, the next moment he will reject and blame you for not liking him. He runs away several times after conflicts, but he always comes back. He is placed in a foster family with a foster father who is experienced, calm, and also able to set clear limits and rules of conduct. After a year, he is able to go to school and play with friends without getting involved in too many conflicts, but he is still very vulnerable in close relations.

3. Insecure disorganized behaviour:
Five-year-old Aurore was severely neglected by a poor 12-year-old teenage mother from birth. She was undernourished when she was found in the street. In the rehabilitation centre, she contacts everybody, and constantly tries to get their attention in a very charming and baby-like way. She wants to sit on the lap of any staff – even any strangers who visit. But her contacts are very short and random, and do not lead to a deeper relation to any particular staff. She doesn’t remember what happened a minute ago. Her ability to attach to a caregiver has not been developed in her first years. She can play with other children, but only for a short while, and she is very easily distracted. After a year in foster care, she is beginning to look for care and protection from her foster parents only, and shows a little affection for them.

የቡድን ውይይት
20 ደቂቃ

  • እነዚህ የመተማመን ስሜት የጎደላቸው ሰውን የመቅረብ ባህርይ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ላይ ሲኖሩ ማወቅ ትችላላችሁ?
  • “ድንጋይ ፊት” ካለው ዲዶ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ህጻናት አይታችኋል? አብዛኛውን ጊዜ ግጭት ውስጥ እንደሚገባው ሮበርት ያሉስ? እንደ አውሮር ከእንክብካቤ ሰጪ ጋር ፍቅር ያለበት ግንኙነት መመስረትን ያልተማሩስ? እባካችሁ ምሳሌዎችን በመስጠት አስረዱን።
  • የመተማመን ስሜት የጎደለው አቀራረብ ካላቸው ህጻናት ጋር የተያያዘ ሥራ በምትሰሩበት ወቅት በጣም ፈታኝ የሚሆንባችሁ ነገር ምንድን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

አሁን ደግሞ፡- የተለያዩ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት የሚያስፈልጋቸው ምን ዓይነት እርዳታ ነው? ሁሉም ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ናቸው ወይስ ከኛ የሚፈልጓቸው እርዳታዎች የተለያዩ ናቸው? መልሶ ማገገም በጣም የሚያስፈልገው ለማን ነው?