ክፍለ ጊዜ 17/21
ገጽ 8/9 የሥራ ዕቅድየሥራ ዕቅድ
ከጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ጋር በተያያዘ ያላችሁን ተሞክሮ እና በአካባቢያችሁ ያለውን ሁኔታ መሠረት በማድረግ ከዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ለእናንተ በጣም አስፈላጊ የሆነው ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ማተኮር ትችላላችሁ። እባካችሁ በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማን፣ እንዴት፣ የት እና መቼ እንደሚሰራ ተወያዩ እንዲሁም ጻፉ፡-
- ወደ እንክብካቤ ከመሸጋገር ጋር በተያያዘ የመልሶ ማገገሚያ ሰራተኞች እና የአደራ አሳዳጊዎች እንዴት አብረው መሥራት እንደሚችሉ?
- የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ስለሚያሳዩአቸው መተማመን በጎደለው መልኩ ሰውን የመቅረብ ባህርያት እና ሰውን የመቅረብ ችግር ካለባቸው ህጻናት ጋር እንዴት መገናኘት እንደሚቻል ይበልጥ መማር? (እባካችሁ ከፌርስታርት /Fairstart/ ፕሮግራም ውስጥ ክፍለ ጊዜ 5 እና 6ን ተመልከቱ)።
- የጎዳና ማህበረሰቡ ውስጥ የግንኙነት መረብ እንዴት እንደምንመሰርት ማቀድ?
- እምነትን መሠረት ካደረጉ እና ማህበረሰብን መሠረት ካደረጉ ሌሎች ድርጅቶች እንዴት የመንፈስ መነሳሳትን ማግኘት እና አብረናቸው መሥራት እንደምንችል ማቀድ።
- በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ግንዛቤ እንዴት ማሳደግ እንደምንችል እና ስለ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት አዎንታዊ አመለካከት መፍጠር እንደምንችል ማቀድ?
ለጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት እንክብካቤ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ለምትሰሩት የሚደነቅ ሥራ ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች እና ፌርስታርት (Fairstart) ያለን ሰዎች መልካም ዕድልን እንመኝላችኋለን!