ክፍለ ጊዜ 17/21
ገጽ 6/9 ህጻናት በጎዳና ላይ ያሏቸው የግንኙነት መረቦችህጻናት በጎዳና ላይ ያሏቸው የግንኙነት መረቦች
ከአዋቂዎች ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት ባሳለፏቸው አሰቃቂ ተሞክሮዎች የተነሳ ጎዳና ቤታቸው የሆነ ህጻናትን በቀጥታ ማግኘት ከባድ እንደሆነ አንድ የምስራቅ አፍሪካ ጥናት ያሳያል። በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ አይቆዩም። የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት በተለያዩ ሰዎች መካከል እዚህ እዚያ ይላሉ፤ አንድ ቦታ ላይ የሚቆዩትም ወዲያው የሚያስፈልጋቸው ነገር እስኪሟላላቸው ብቻ ነው። አንድ ቅጽበት ላይ ጓደኝነት ፍለጋ ወደ እኩዮቻቸው ይሄዳሉ፤ በሚቀጥለው ቅጽበት ደግሞ ከአንድ አዋቂ ትንሽ ምግብ ያገኛሉ፤ የሚተኙበት ቦታ ያገኛሉ፣ ወዘተ። እነዚህ ፈጣን ግንኙነቶች የወላጅ እንክብካቤን እንደሚተካ ሰንጠረዥ ናቸው።
ጎዳናን ቤቱ ያደረገን ህጻን እንዲያምነን ማድረግ ረጅም ሂደት አለው። አንደኛው ጥሩ መነሻ ቦታ ህጻናቱን አስቀድመው ከሚያውቋቸው ጎዳና ላይ ያሉ ሰዎች (ጎዳና ላይ ዕቃዎችን የሚሸጡ ሰዎች፣ ፖሊሶች፣ መካኒኮች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ በጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምድቦች ውስጥ መደበኛ ባልሆነ መልኩ መሪ የሆኑ ወጣቶች እና ሌሎች ጎዳና ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ግንኙነት መመስረት ነው። በእነዚህ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ካገኛችሁ በጣም እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት የትኞቹ እንደሆኑ በመለየት ያግዟችኋል እንዲሁም ከእነሱ ጋር ያስተዋውቋችኋል። ይህም በአጠቃላይ ማህበረሰቡ ውስጥ መልሶ ማገገም የሚያስፈልጋቸውን ህጻናት ለማግኘት እና ለመርዳት የሚያስችል ግንዛቤን ለመፍጠር ያስችላችኋል።
- በጎዳና ላይ ካሉት ማህበረሰባችን ውስጥ ልናነጋግራቸው የሚገባን ሰዎች እነማን ናቸው? – አነስተኛ ሻጮች፣ ፖሊሶች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ኢ-መደበኛ መሪዎች፣ ሌሎች? በጣም ወሳኝ የሆነው ማን ነው?
- በተጨባጭ የወላጅ እንክብካቤን ያጡ ህጻናትን እንድናገኝ እንዲያግዙን የምንጠይቃቸው እንዴት ነው?
የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ቡድኖች የሚከተሉት ሁለት ገጽታዎች አሏቸው፡- በአንድ በኩል ረሀብ እና እንክብካቤ ማጣት ህጻናት የሚሰርቁ፣ የሀይል ጥቃቶችን የሚፈጽሙ፣ ዕጾችን የሚነግዱ፣ በጣም ደካማ የሆኑት አባሎቻቸው ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚፈጽሙ፣ ወዘተ የወንጀል ቡድኖችን እንዲፈጥሩ ሊያስገድዷቸው ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ቡድኖች ለእያንዳንዱ አባላቸው ጥበቃ ያደርጋሉ፣ ወሳኝ መረጃዎችን ይለዋወጣሉ፣ ከመሀላቸው ለታመሙ ወይም በዕድሜ ትንሽ ለሆኑ ልጆች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ያሟላሉ እንዲሁም አደጋዎችን በተመለከተ እርስ በእርስ ማስጠንቀቂያ ይሰጣጣሉ። ቻይ መሆን እና ወንጀሎችን የሚፈጽሙት ወላጆቻቸው ባለመኖራቸው እና የእነሱን እንክብካቤ እና አመራር በማጣታቸው እንደሆነ መገንዘብ ይኖርባችኋል። የሆነው ሆኖ ግን በጎዳና ላይ የአቻ ቡድኑ ውስጥ አባል ያልሆነ ህጻን ለረጅም ጊዜ በህይወት አይቆይም። የአቻ ቡድኖች የሚደራጁት እንዴት ነው፤ በእነሱ አማካኝነት አንድን ህጻን ማግኘት የምትችሉትስ እንዴት ነው?
የእነዚህ ቡድኖች መሪዎች አብዛኛውን ጊዜ በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆች ወይም የብዙ ዓመት የጎዳና ልምድ ያላቸው ወጣቶች ናቸው። ሌሎች መሪዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ እነዚህ መሪዎች የዕለት ተዕለት ህይወትን ያደራጃሉ እንዲሁም አብሮ ለመሥራት የሚያስፈልጉ ሕጎችን ያስቀምጣሉ። ካማንጉ የአመራር ተሞክሮውን እንደሚከተለው ገልጾታል፡- “ጎዳና ላይ ለመኖር አንድ ሰው የበሰለ እና ጠንካራ መሆን አለበት እንዲሁም እርስ በእርስ የምናወጣቸውን ሕጎች መከተል አለበት። እንደደዚያ ካልሆነ ማዕከላት ውስጥ ነው መኖር ያለበት። ጎዳና ለደካማ ህጻናት አይሆንም”። ከእነዚህ ህጻናት ውስጥ አንዳንዶቹ አዋቂ በሚሆኑበት ጊዜ በማህበረሰባቸው ውስጥ ወሳኝ ለውጥ አምጪዎች ይሆናሉ እንዲሁም አሉታዊ ተሞክሮዎቻቸውን ኃላፊነት ወደተሞላባቸው ማህበራዊ ሥራዎች ይለውጧቸዋል።
- በማህበረሰባችሁ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ የጎዳና ቡድን መሪዎች እነማን ናቸው?
- ልናገኛቸው እና እንዲያምኑን ልናደርጋቸው የምንችለው እንዴት ነው?
- ለሚሰጡት እንክብካቤ እና አመራር አክብሮት ልናሳያቸው እና ድጋፋቸውን ልናገኝ የምንችለው እንዴት ነው?
- በአካባቢያችሁ ባሉ ዕምነትን መሠረት ያደረጉ ወይም ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች ውስጥ ከጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ጋር የተያያዘ ሥራ የሚሰሩት የትኞቹ ሰዎች ናቸው? በጋራ ስብሰባ ለማድረግ እንጋብዛቸው፤ ወይስ የሚሰሩበት ቦታ ላይ ፈልገን እናግኛቸው?
እባካችሁ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን በአጭሩ አዘጋጁ፣ ተስማሙባቸው እንዲሁም ጻፏቸው፡- በጎዳና ላይ ካሉ ቁልፍ ሰዎች፣ ከጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ቡድን መሪዎች እና በማህበረሰባችን ውስጥ ካሉ ሌሎች ድርጅቶች ጋር መገናኘት የምንችለው እንዴት ነው? የራሳችን መሪዎች ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው የትኞቹን ጉዳዮች በተመለከተ ነው፣ ግንኙነቶች ላይ የሚሰራው ማን ነው፣ የመልሶ ማገገም ሠራተኞችስ በጋራ መተማመን ላይ የተመሰረተ የግንኙነት መረብ መመስረት የሚችሉት እንዴት ነው?